የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ በ"ክህደት" ወንጀል በሞት እንዲቀጡ ባለተገኙበት ተፍረደባቸው
20:03 30.09.2025 (የተሻሻለ: 20:14 30.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ በ"ክህደት" ወንጀል በሞት እንዲቀጡ ባለተገኙበት ተፍረደባቸው
ከዚህ ቀደም የሰራዊቱ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጆሴፍ ካቢላን የሕይወት ዘመን እንደራሴነት ያለመከሰስ መብት እንዲነሳላቸው ለሴኔቱ በይፋ በመጠየቅ "የጦር ወንጀሎችን፣ በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን እና የጅምላ ጭፍጨፋዎችን" የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ጠቅሷል።
ለአመፅ ድጋፍ በማድረጋቸው የተከሰሱት ሙታምባ ካቢላ ወደ አገራቸው ተመልሰው ለፍርድ እንዲቀርቡ በማሳሰብ በሌሉበት ሊፈረድባቸው እንደሚችል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውም ይታወሳል።
ከ2023 መጨረሻ ጀምሮ ከአገራቸው የፈረጠጡት ካቢላ አብዛኛውን ጊዜ ኑሮአቸውን በደቡብ አፍሪካ ሲያደርጉ፣ ከ2 አሥርት ዓመታት የሥልጣን ቆይታ በኋላ በጎርጎሮሳውያኑ 2018 ከሥልጣን ወርደዋል፡፡ አገራቸው ውስጥ ባይኖሩም ከወራት በፊት ወደ አገር ቤት ተመልሰው በምስራቅ ኮንጎ ያለውን ቀውስ ለመፍታት ለመርዳት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።
ካቢላ በ2001 አባታቸው ከተገደሉ በኋላ ወደ ሥልጣን መጥተዋል። የሥልጣን ዘመናቸው በ2016 ሲያበቃ ከሥልጣን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ወደ አሰቃቂ ተቃውሞዎች ያመራ ሲሆን፣ በመጨረሻም ከ2018 ምርጫ በኋላ ከሥልጣን ወርደዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X