የናይል ሀገራት ትብብር ኢንሺየቲቭ የውሃ ጥራትን ለመለካት የሚያስችሉ መሣሪያዎችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየናይል ሀገራት ትብብር ኢንሺየቲቭ የውሃ ጥራትን ለመለካት የሚያስችሉ መሣሪያዎችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገ
የናይል ሀገራት ትብብር ኢንሺየቲቭ የውሃ ጥራትን ለመለካት የሚያስችሉ መሣሪያዎችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.09.2025
ሰብስክራይብ

የናይል ሀገራት ትብብር ኢንሺየቲቭ የውሃ ጥራትን ለመለካት የሚያስችሉ መሣሪያዎችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገ

መሣሪያውቹ ከ169 ሺ ዶላር በላይ የሚያወጡ መሆናቸውን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የውሃ ሀብት በጥራትና በመጠን ክትትል ማድረግ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራትም ጠቃሚ መሆኑን ገልፀው የተደረገው ድጋፍም የኢትዮጵያን ወንዞች የጥራት መረጃ ለማሰባሰብ እና ለመጠቀም ተጨማሪ መሣሪያዎችን እንድናገኝ ያነሳሳናል ብለዋል።

የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ፍሎረንስ ግሬስ ለኢትዮጵያ ድጋፉ የናይል ተፋሰስ አገሮች ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳይና የናይል ውሃ ንጹህ፣ ዘላቂና የመጭውን ትውልድ የኑሮ ደረጃ ማሻሻል የሚችል  እንዲሆን ነው ብለዋል።

የውሃ ጥራት መለኪያ መሳሪያዎቹ በተገቢው መንገድ ለአገልግሎት እንዲበቁ ለላብራቶሪ ቴክንሺያኖችና ለሀይድርሎጂስት ባለሙያዎች በቀጣዩቹ ሦስት ቀናት ሥልጠና ይሰጣል ሲል የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0