የናይጄሪያ ወታደሮች የወንበዴዎች ጥቃትን አከሸፉ፤ የጦር መሳሪያዎችንም ወረሱ
16:58 30.09.2025 (የተሻሻለ: 17:04 30.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የናይጄሪያ ወታደሮች የወንበዴዎች ጥቃትን አከሸፉ፤ የጦር መሳሪያዎችንም ወረሱ
በ"ኦፕሬሽን ዊርል ስትሮክ" ስር ያሉ ወታደሮች ከመስከረም 16 እስከ 18 በተደረገው ዘመቻ ፤ በቤኑኤ ክፍለ ሀገር ውስጥ በካቲሲና-አላ የታቀዱ የወንበዴዎች ጥቃቶችን እንዳከሸፉ የኦፕሬሽኑ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
ከተወረሱት ዕቃዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
🟠 ጠመንጃ (ሽጉጦች)፣
🟠 ጥይቶች፣
🟠 መጽሔቶች (የጥይት ማስቀመጫዎች)፣
🟠 የእጅ ቦምብ ፣
🟠 የአስለቃሽ ጭስ ጋዝ ታንከር፣
🟠 የሕክምና መሣሪያዎች እና
🟠 30 ተንቀሳቃሽ ስልኮች።
የዘመቻው አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ሙሴ ጋራ የወታደሮቹን ፈጣን እርምጃ ያደነቁ ሲሆን፣ በቤኑኤ እና በአጎራባች ግዛቶች ሰላምን ለማስመለስ ያላቸውን ቁርጠኝነት አጽንኦት ሰጥተዋል።
አክለውም ነዋሪዎች የደህንነት ጥረቶችን ለመደገፍ ወቅታዊ መረጃዎችን ማቅረባቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
🪖 እ.ኤ.አ. በ2018 የተጀመረውዘመቻ የትጥቅ ቡድኖችን ለመዋጋት ወታደሩን፣ ፖሊስን እና ዲኤስኤስ (የሀገር ውስጥ ደኅንነት አገልግሎትን) ያቀፈ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


