ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የሱዳንን ጎርፍ ለመቀነስ ረድቷል ስትል አስታወቀች
16:24 30.09.2025 (የተሻሻለ: 16:34 30.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የሱዳንን ጎርፍ ለመቀነስ ረድቷል ስትል አስታወቀች
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ በትናንትናው ዕለት ሲናገሩ፦ “በሱዳን ያለው ጎርፍ ከነጭ ዓባይ ሊሆን ይችላል። ሕዳሴ ግድብ ባይኖር ኖሮ፣ መጠኑ አውዳሚ ሊሆን ይችል ነበር። ሕዳሴ ግድብ አደጋውን ለመቀነስ ትልቅ ሚና ተጫውቷል” ብለዋል።
ሱዳን ቅዳሜ ዕለት በዋና ዋናዎቹ የዓባይ ወንዝ ገባር ወንዞች፣ በጥቁር ዓባይ እና በነጭ ዓባይ፣ የውሃ መጠን እየጨመረ መምጣቱን በመጥቀስ የጎርፍ አደጋ ማስጠንቀቂያ አውጥታ ነበር። ባለሥልጣናቱ ማስጠንቀቂያውን ሰኞ ዕለትም አስቀጥለውታል።
የሱዳን መስኖ ሚኒስቴር እሁድ ምሽት ላይ በዚያ አካባቢ የሚገኙ ግድቦች ከመጠን ያለፈ ውሃ በመልቀቃቸው የውሃው መጠን ለአራት ተከታታይ ቀናት ከፍተኛ እንደነበር አስታውቋል ሲሉ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ጉዳዩን አስመልክቶ የተጠየቁት የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ “ትርፍ ውሃ አልለቀቅንም” ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X