ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ የካርበን ክሬዲት ሽያጭን እያሰፋች መሆኑን አስታወቀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ የካርበን ክሬዲት ሽያጭን እያሰፋች መሆኑን አስታወቀች
ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ የካርበን ክሬዲት ሽያጭን እያሰፋች መሆኑን አስታወቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.09.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ የካርበን ክሬዲት ሽያጭን እያሰፋች መሆኑን አስታወቀች

ሀገሪቱ 15 ሚሊዮን ቶን የካርቦን ዳይኦክሳይድ ክሬዲቶችን ለመሸጥ ያላትን እቅድ በኒውዮርክ በተካሄደው 80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት አስታውቃለች።

የአረንጓዴ አሻራ ቴክኒካል ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አደፍርስ ወርቁ እንደተናገሩት፤ አገሪቱ ከፋርም አፍሪካ ለካርበን ፕሮጀክት 12 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያገኘች ሲሆን፣ ከዓለም ባንክ ጋር ደግሞ የ40 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የካርበን ሽያጭ ስምምነት ተፈራርማለች።

ከዚህም በተጨማሪ ኖርዌይ ከኦሮሚያ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከጋምቤላ እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ጨምሮ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች 75 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የካርበን ክሬዲቶችን ገዝታለች።

እ.ኤ.አ. ከ2019 ጀምሮ ከ20 ቢሊዮን በላይ ዛፎችን የተከለው የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ፤ ለካርበን ክሬዲት ስትራቴጂዋ ወሳኝ መሆኑን አደፍርስ አጽንዖት መስጠታቸውን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0