ኢትዮጵያ ማኅበራዊ ጥበቃን መሠረታዊ መብትና ለዘላቂ ልማት መሠረት አድርጋ ትመለከተዋለች - የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
15:15 30.09.2025 (የተሻሻለ: 15:24 30.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ማኅበራዊ ጥበቃን መሠረታዊ መብትና ለዘላቂ ልማት መሠረት አድርጋ ትመለከተዋለች - የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ማኅበራዊ ጥበቃን መሠረታዊ መብትና ለዘላቂ ልማት መሠረት አድርጋ ትመለከተዋለች - የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
ኤርጎጌ ተስፋዬ “የማኅበራዊ ጥበቃ ለዘላቂ ልማት እና ደህነት" በሚል ርዕስ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለተወጣጡ ሠልጣኞች የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የሥልጠና መርሃ ግብርን አስጀምረዋል።
ሥልጠናው ትኩረቱን የማኅበራዊ ጥበቃ ሥርዓቶችን ለማጠናከር በሚረዱ ፈጠራ ባላቸው የፋይናንስ ዘዴዎች እና ቴክኒካዊ አቀራረቦች ላይ ያደረገ ሲሆን፣ መንግሥታት እና የልማት ባለሙያዎች የሚያጋጥሟቸውን ቁልፍ ተግዳሮቶችንም ይመለከታል ተብሏል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የማኅበራዊ ጥበቃ ለብሔራዊ ልማት ብቻ ሳይሆን፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እና ከሰብዓዊ ደህንነት ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፉን አጀንዳ በመቅረጽ ረገድ ወሳኝ መሆኑን ያረጋግጣል።
መርሃ ግብሩ ከኢትዮጵያ ጨምሮ ከሞዛምቢክ፣ ከሩዋንዳ፣ ከዚምባብዌ እና ከሌሎች ሀገራት የተውጣጡ ተወካዮችን አሰባስቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
