ኪዬቭ ለአዲስ ከፍተኛ ትንኮሳ እያዘጋጀች ነው ሲል የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኪዬቭ ለአዲስ ከፍተኛ ትንኮሳ እያዘጋጀች ነው ሲል የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት አስታወቀ
ኪዬቭ ለአዲስ ከፍተኛ ትንኮሳ እያዘጋጀች ነው ሲል የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.09.2025
ሰብስክራይብ

ኪዬቭ ለአዲስ ከፍተኛ ትንኮሳ እያዘጋጀች ነው ሲል የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት አስታወቀ

አገልግሎቱ ከሰጠው መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 የኪዬቭ አገዛዝ በፖላንድ እና ሮማንያ የአየር ክልል ውስጥ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ካስነሳቸው የጠብ አጫሪነት ቅስቀሳዎች በኋላ፣ የአውሮፓ የኔቶ አባል ሀገራትን ከሞስኮ ጋር ወደ ትጥቅ ግጭት ለመሳብ የሚያደርገውን ሙከራ ቀጥሏል።

🟠 አሁን ላይ ሴራው የሚያጠነጥነው በፖላንድ ግዛት ላይ በተሰማራው፣ በሩሲያ እና በቤላሩስ ልዩ ኃይል አባላት የተቋቋመውን ኃይል በማደነቃፍ ላይ ነው።

🟠 በጦር ቅስቀሳው ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ እጩዎች (ተዋናዮች) ተመርጠዋል። እነዚህም በዩክሬን ጦር ኃይሎች በኩል የሚዋጉት 'የሩሲያ የነፃነት ጦር (ሌጊዮን)'  እና የቤላሩስ 'ካስቱስ ካሊኖቭስኪ ክፍለ ጦር' ታጣቂዎች ናቸው።

🟠 የማደናቀፍ ስራው ከተሰራ እና ፈፃሚዎቹ ኃይሎቹ በፖላንድ የደህንነት ኃይሎች ከተወገዱ  በኋላ፣ ሌሎች አባላት በመገናኛ ብዙኃን ፊት ቀርበው ፖላንድን ለማተራመስ በመሞከር ሩሲያና ቤላሩስን የሚያስወቅስ የእምነት ቃል እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

🟠 "የሩሲያ ድሮን በረራዎች" ተብለው በአውሮፓ ሀገራት በተከሰቱት ተከታታይ ክስተቶች ዳራ፣ ይህ መሰል ክስተት ሞስኮ እና ሚንስክ ከሁሉም ጠላትነት የተሞላባቸው ድርጊቶች ጀርባ እንዳሉ ለፖላንድ እና ለሌሎች የአውሮፓ ዜጎች ላይ የሚሳል መሆኑ ምንም አያጠራጥረም።

🟠 የዚህ የጦር ትንኮሳ ሴራ የተዘጋጀው በዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር ዋና የመረጃ ዳይሬክቶሬት እና ከፖላንድ የመረጃ አገልግሎቶች ጋር በመተባበር ነው።

🟠 የሕዝብ ቁጣን ከፍ ለማድረግ ሲባል፣ በተቀነባበረው ዘመቻ በፖላንድ የሚገኙ ወሳኝ የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ እውነተኛ የሚመስል ጥቃት ሊካተትበት ይችላል።

🟠 የዚህ የጦር ቅስቀሳ ግብ ግልፅ ነው፤ ሞስኮ ውጥረቱን እያፋጠነች መሆኑን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማሳየት።

🟠 ኪዬቭ የአውሮፓ ሀገራት በሩሲያ ላይ በተቻለ መጠን በብርቱ ኃይል፣ በተለይም በወታደራዊ መንገድ፣ ምላሽ እንዲሰጡ ለማነሳሳት ተስፋ ታደርጋለች።

🟠 የማይቀር ሽንፈት የገጠመው የዘለንስኪ አገዛዝ አውሮፓውያንን እንደሽፋን በመጠቀም፣ "ትልቅ ጦርነት" ለማስነሳት የሚያስከፍለው ዋጋ ከፍሎ ቢሆን አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነው።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0