ዓለምአቀፍ የትርጉም ቀን በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን እየተከበረ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዓለምአቀፍ የትርጉም ቀን በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን እየተከበረ ነው
ዓለምአቀፍ የትርጉም ቀን በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን እየተከበረ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.09.2025
ሰብስክራይብ

ዓለምአቀፍ የትርጉም ቀን በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን እየተከበረ ነው

የኮሚሽኑ የቀጣናዊ ትስስርና የንግድ ዲቪዥን ተጠባባቂ ዳይሬክተር እና የአፍሪካ የንግድ ፖሊሲ ማዕከል አስተባባሪ ዶ/ር መላኩ ደስታ የኮሚሽኑን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴን ወክለው ባደረጉት ንግግር ትርጉም የማኅበረሰቡ ሥነ ልሳናዊና ባሕላዊ ማንነቶች የሚጠበቁበት ነው ብለዋል።

“ተርጓሚዎችንም በማኅበረሰቡ ሞራላዊ እና ቁሳዊ ሀብቶች ጠባቂነት አወድሰዋል። ቀኑ ይህንኑ የተርጓሚዎችን ሚና ለማወደስና እውቅና ለመስጠት እንደሚከበርም ተናግረዋል።”

ቀኑ ትርጉምና ተርጓሚዎች እንዲሁም የቋንቋ ልሂቃን ቋንቋንና ባህልን በማሳደግ፣ ማኅበረሰብን በማቀራረብና ማኅበራዊ መስተጋብርን በማጠናከር እንዲሁም እውቀትን በማሸጋገርና እንደ ቅርስ ጠብቆ በማቆየት የሚጫወቱትን ሚና ታሳቢ በማድረግ የሚከበር ነው።

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጄኒ ቴሬኪንን ጨምሮ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የቋንቋ ምሁራን፣ የትርጉም ባለሙያዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በአከባበር ሥነ ስርዓቱ ተገኝተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
ዓለምአቀፍ የትርጉም ቀን በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን እየተከበረ ነው - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
ዓለምአቀፍ የትርጉም ቀን በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን እየተከበረ ነው - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0