ዓመታዊ የዋጋ ግሽበት በነሐሴ 2017 ዓ.ም መጨረሻ 13.6 በመቶ መድረሱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዓመታዊ የዋጋ ግሽበት በነሐሴ 2017 ዓ
ዓመታዊ የዋጋ ግሽበት በነሐሴ 2017 ዓ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.09.2025
ሰብስክራይብ

ዓመታዊ የዋጋ ግሽበት በነሐሴ 2017 ዓ.ም መጨረሻ 13.6 በመቶ መድረሱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

ምግብ ነክ የዋጋ ግሽበት ነሐሴ ወር 2017 ዓ.ም መጨረሻ 12.7 በመቶ የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ከነበረው የ18.8 በመቶ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ቅናሽ ማሳየቱን ገልጿል፡፡

ምግብ ነክ ያልሆነ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር መጠነኛ ጭማሪ በማሳየት 15.1 በመቶ ሆኗል፡፡ ለዚህም በቅርቡ የተካሄደው የውጭ ምንዛሪ ተመን ለውጥ ጫና በተወሰነ መልኩ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተጠቁሟል፡፡

መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም ስብሰባውን ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ፣ ለዋጋ ግሽበት መቀነስ ዐበይት ምክንያቶችን አስቀምጧል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ተግባራዊ እያደረገ ያለው ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ፣

የግብርና ምርታማነት መሻሻል እና

መንግሥት ዋጋን ለማረጋጋት እየወሰዳቸው ያሉ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ናቸው፡፡

እንደ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ፣ ነሐሴ ወር 2017 ዓ.ም መጨረሻ ወርሃዊ የዋጋ ግሽበት ወደ 11 በመቶ ዝቅ ማለቱ፣ የዋጋ ግሽበቱ በኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ እየቀለለ መሄዱን ያመላክታል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0