የቅኝ ገዢዎች ውሸት፣ የአርበኞች እውነታ፡ ኢትዮጵያ ከፋሺስት ኢጣሊያ ጋር የገጠመችው የትርክት ጦርነት

የቅኝ ገዢዎች ውሸት፣ የአርበኞች እውነታ፡ ኢትዮጵያ ከፋሺስት ኢጣሊያ ጋር የገጠመችው የትርክት ጦርነት
ሰብስክራይብ
የዛሬው የድረም ኦፍ ቼንጅስ ዝግጅታችን አመታትን ወደኋላ መለስ ብሎ ከጣልያን ወራሪ ኃይል ጋር ከጦር አውድማ ባሻገር የተደረገን የተደረገን የፕሮፓጋንዳ ትንቅንቅ ይቃኛል፡፡ ፋሽስት ኢጣልያ ለጠብ አጫሪ እንቅስቃሴው ምክንያት፡ ኢትዮጵያን ስልጣኔ የማያዉቃት አድርጎ ለመሳል ሞክሯል፡፡ ኢትዮጵያውያንም በአጸፋው አቤቱታቸውን ለዓለም ምንግስታት በዲፕሎማሲ ከማሰማት በዘለለ፣ የቀደምት ስልጣኔ ባለቤት ስለመሆናቸው ከነመገለጫዎቻቸው አብነት በድርገውና ወራሪውን ቅኝ ገዥ እንዳመጣጡ በትርክት ጦር ሜዳም ተፋልመዋል። የድል ታሪኮቻቸዉንም ከትበዋል።

“የኢጣሊያ ፕሮፓጋንዳ የታለመው ለአውሮፓውያን እንጂ ለኢትዮጵያውያን አልነበረም። የቅኝ ግዛት ዘመቻው የሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባል በሆነች ሀገር ላይ የተደረገ ትግል ሳይሆን፣ አጭር የቅኝ ግዛት ጦርነት እንደሆነ ለማሳየት ብቻ ነበር። ነገር ግን ኢትዮጵያ ከማይጨው ጦርነት በፊት የአርበኝነት ጦርነትን ይፋ አደረገች – ይህ ተቃውሞም የሉዓላዊነታችን የጀርባ አጥንት ሆነ።” ሲሉ የታሪክ ምሁርና ጸሃፊ ጥላሁን ጣሰዉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

ከአርበኞች የመረጃ ልውውጥ ጀምሮ እስከ ንጉሠ ነገሥቱ የጄኔቫ ንግግር ድረስ፣ ኢትዮጵያ ወታደራዊ፣ ባህላዊና የመገናኛ መሳሪያዎችን ሁሉ ተጠቅማ ፣ ታሪኳንና የተቃጣባትን የትርክት ጦርነት ለመቀልበስ የቅኝ ገዢዎችን ፕሮፓጋንዳና ግብዝነት ለማጋለጥ ተነሳች ።
🔊 በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ ፕሮግራም ያዳምጡ:
አዳዲስ ዜናዎች
0