የናይጄሪያ የድፍድፍ ነዳጅ ምርት መጨመሩ ተገለፀ
20:32 29.09.2025 (የተሻሻለ: 20:34 29.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የናይጄሪያ የድፍድፍ ነዳጅ ምርት መጨመሩ ተገለፀ
የናይጄሪያ ነዳጅ ምርት በቀን ወደ 1.8 ሚሊዮን በርሜል ማደጉን የሀገሪቱ የነዳጅ ሀብት ሚኒስትር ሄይኒከን ሎክፖቢሪ በኒውዮርክ በተካሄደው የአፍሪካ ኢነርጂ ኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ አስታውቀዋል።
በመስከረም 2024፤ ናይጄሪያ በቀን 1.3 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ማምረት መቻሏን የኦፔክ መረጃ ያሳያል።
የኢኳቶሪያል ጊኒ ተወካይ አንቶኒዮ ኦቡሩ ኦንዶ የኢነርጂ ባንክ በማቋቋም እና የሀገር ውስጥ ገንዘብ በማሰባሰብ አፍሪካ በኃይል ዘርፏ ላይ የበለጠ ቁጥጥር እንድታደርግ በጉባዔው ላይ ጥሪ አቅርበዋል።
የአፍሪካ የነዳጅ አምራቾች ድርጅት ዋና ጸሐፊ ኦማር ፋሩክ ኢብራሂም በበኩላቸው፤ የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ለአፍሪካ የኃይል የወደፊት ዕጣ ፈንታ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ቁልፍ መድረክ ማመቻቸቱን አክለው ገልጸዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X