በኢትዮጵያ የኒውክሌር ሕክምናን ማስፋት አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ነው - የኒውክሌር ሕክምና ስፔሻሊስቶች
19:57 29.09.2025 (የተሻሻለ: 20:04 29.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የኒውክሌር ሕክምናን ማስፋት አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ነው - የኒውክሌር ሕክምና ስፔሻሊስቶች
የኒውክሌር ሕክምና በተለይ ለካንሰር በሽታ ሕክምና ውጤታማነት የላቀ አስተዋጽኦ ቢኖረውም፤ በኢትዮጵያ አገልግሎቱን የሚሰጡ ተቋማት ቁጥር ከሁለት እንደማይበልጥ ዶክተር ኪሩቤል ተስፋዬ ይናገራሉ።
ዶክተር ኪሩቤል በኢትዮጵያ ገና በመዳህ ላይ የሚገኘውን ይህን ዘርፍ ለማሳደግ፤ በመንግሥት የተሰጠው ትኩረት ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ አሳስበዋል።
የሙያ አጋራቸው ዶ/ር ታከለ ሎዳሞ በበኩላቸው፤ ዘርፉ የሕክምና አስተዳደርን ከ30 እስከ 50 በመቶ የመቀየር አቅም እንዳለው አንስተዋል።
"ይህ ማለት የኒውክሌር ሕክምና ከሦስት ታካሚዎች የአንዱን፤ ከፍ ሲልም የግማሹን የሕክምና አሰጣጥ መንገድ የመቀየር አቅም አለው እንደማለት ነው። ሌላው ሕክምናው በሀገራችን መስፉቱ አገልግሎቱን ለማግኘት ህሙማንን ወደ ሌሎች ሀገራት ሪፈር የምናደርግበትን ሁኔታ ያስቀራል" ሲሉም ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X