አፍሪካ በዓለም ላይ ካሉ በርካታ የውሳኔ መስጫ ማዕከላት ተገፍታለች - የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
አፍሪካ በዓለም ላይ ካሉ በርካታ የውሳኔ መስጫ ማዕከላት ተገፍታለች - የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
በአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተመድ 80ኛ ጉባዔ የተነሱ ቁልፍ ነጥቦች፦
ፍልስጤም
እስራኤል በጋዛ ላይ የከፈተችው ጦርነት የዘር ማጥፋት እና በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች በማለት አውግዘዋል።
በ1967ቱ ድንበር ምስራቅ እየሩሳሌምን ዋና ከተማዋ ለሚያደርግ የፍልስጤም መንግሥት ድጋፍ ሰጥተዋል።
ፍልስጤም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሙሉ አባል እንድትሆን እና ሕዝቦቿ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።
ዓለም አቀፍ ሕግን በመተግበር ላይ የሚታየውን ድርብ መስፈርት ተችተዋል።
ምዕራብ ሰሃራ
ምዕራብ ሰሃራ በአፍሪካ የመጨረሻዋ ቅኝ ግዛት ናት ብለዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰሃራዊያን ሕዝብን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንዲያስከብር ጠይቀዋል።
“የቀጠለውን” የሞሮኮ ወረራ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አውግዘዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ማሻሻያ እና ዓለም አቀፍ ፍትሕ
የተባበሩት መንግሥታት በ80ኛ ዓመቱ ስንኩሉነቱንና ድርብ መስፈርቶችን ማስወገድ አለበት።
አፍሪካ ፍትሐዊ ውክልና እንድታገኝ በፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።
ክልላዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች
በሊቢያ፣ ሱዳን፣ ማሊ እና ሳህል ቀጣና ውስጥ ሰላማዊ መፍትሄዎች እንዲገኙ ተጠይቋል።
የውጭ ጣልቃ ገብነት እና የአፍሪካ "እጀ አዙር-ቅኝ ግዛት" ብዝበዛ ውድቅ ተደርጓል።
ኩባ በአሜሪካ ማዕቀብ ዙሪያ ድጋፍ አግኝታለች፤ በተናጥል የሚጣሉ ማዕቀቦች እንዲያቆሙም ጥሪ ቀርቧል።
ሽብርተኝነት እና ፅንፈኝነት ተወግዘዋል፤ እነሱን ለማጥፋት ዓለም አቀፍ ትብብር እንዲደረግ ተጠይቋል።
ልማት እና ትብብር
በታዳሽ ኃይል፣ በምግብ ዋስትና እና በደቡብ-ደቡብ ትብብር ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ጎላ ተደርገው ታይተዋል።
ለጋራ ልማት፣ መረጋጋት እና ውህደት "አዲስ የሜዲትራኒያን አጋርነት" የተሰኝ የትብብር ጥሪ ቀርቧል።
የማጠቃለያ እይታ
አልጄሪያ ከፍልስጤም እስከ ምዕራብ ሰሃራ ከሚገኙ የተጨቆኑ ሕዝቦች እና ከአፍሪካ የለውጥ ጥሪ ጋር በጋራ ተሰልፋለች።
እውነተኛ የባለብዙ ወገን ትብብር እኩልነትን፣ ፍትሕን እና የሕዝቦችን የነፃነትና ክብር መብት መጠበቅ እንደሚጠይቅ ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X