ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ማስተዳደር መቻሏ ከፍተኛ ክብር ያጎናፅፋታል - የኒውክሌር ፊዚክስ መምህር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ማስተዳደር መቻሏ ከፍተኛ ክብር ያጎናፅፋታል - የኒውክሌር ፊዚክስ መምህር
ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ማስተዳደር መቻሏ ከፍተኛ ክብር ያጎናፅፋታል - የኒውክሌር ፊዚክስ መምህር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.09.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ማስተዳደር መቻሏ ከፍተኛ ክብር ያጎናፅፋታል - የኒውክሌር ፊዚክስ መምህር

የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ የሚኖረው ከፍተኛ አስተማማኝነት፤ የተጀመረውን ውጥን እውን ለማድረግ በቂ ምክንያት ይሆናል ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኒውክሌር ፊዚክስ መምህር ረ/ፕሮፌሰር ጥላሁን ተስፋዬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

"እኛ ኢትዮጵያውያን ከአንድ ወር በፊት ከነበርንበት ከፍ ባለ መንፈስ ላይ ነን። ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከፍተኛ መንፈሳዊ ከፍታን፣ የክብር ስሜት አምጥቷል። የግድቡ መመረቅ ‘አሳካነው’ የሚል ስሜት አምጥቷል። በተመሳሳይ መልኩ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ይበልጥ የተራቀቀ፣ ይበልጥ የላቀ ነው። በኢትዮጵያ ምድር እውን ሲሆን ወጣቱን ትውልድ በከፍተኛ ደረጃ ያነሳሳል፤ ሳይንስም በሕዝቡ ዘንድ በተሻለ ሁኔታ ተቀባይነት ያገኛል" ብለዋል።

በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል የተፈፀመውን ስምምነት ያነሱት ረ/ፕሮፌሰር ጥላሁን፤ ሮሳቶም የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎችን ከመትከል አንስቶ የሰው ኃይል በማሠልጠን እና የኒውክሌር መሠረተ ልማት በማልማት ልምድ ስላለው ተመራጭ አድርጎታል ብለዋል፡፡

“ይህ ትብብር ወደ አጠቃላይ የስትራቴጂክ አጋርነት ሊያድግ ይችላል፡፡ በተለይም በኢነርጂ፣ ሳይንስ፣ ግብርና፡፡ ለእንደኔ ላሉት መምህራን ደግሞ በትምህርት ዘርፍ ጥሩ እድል ይሆናል፡፡ ለዓመታት ስናስተምር የነበረው ነገር እውን መሆን የሚችልበትም ነው፡፡”

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0