አዲስ የህጻናትና ወጣቶች ዘመናዊ የኪነጥበብ ማዕከል በአዲስ አበባ ተመረቀ
18:14 29.09.2025 (የተሻሻለ: 18:24 29.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አዲስ የህጻናትና ወጣቶች ዘመናዊ የኪነጥበብ ማዕከል በአዲስ አበባ ተመረቀ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኪነጥበብ እሴቶችን ለማጎልበት፣ ስልጣኔን ለማፋጠን እና ማህበረሰባዊ ትርክትን ለመቅረጽ ወሳኝ መሳሪያ መሆኑን በመገንዘብ ማዕከሉ መገንባቱን ተናግረዋል፡፡
ሕንጻው የኪነጥበብን ኃይል ለሀገር ግንባታና ለትውልድ ለውጥ ለመጠቀም ቁርጠኛ እንደሆንን ማሳያ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ 110 ፕላዛዎችና ከ50 በላይ የአምፊቲያትር ቦታዎች መገንባታቸንም አስታውቀዋል።
አዲስ የተመረቀው የቴዓትር ማዕከል፦
በሁለት 14 ፎቅ ህንጻዎች ውስጥ የሚገኝ፣
1 ሺህ 200 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው የቴአትር አዳራሽ፣
ሁለት የሲኒማ አዳራሾችና የተለያዩ ልዩ የአገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ያሉት ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X



