በሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት ሄሊኮፕተር በአሸባሪዎች ተያዘ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት ሄሊኮፕተር በአሸባሪዎች ተያዘ
በሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት ሄሊኮፕተር በአሸባሪዎች ተያዘ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.09.2025
ሰብስክራይብ

በሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት ሄሊኮፕተር በአሸባሪዎች ተያዘ

አውሮፕላኑ በግዳጅ እንዲያርፍ ከተደረገ በኋላ የአል-ቃይዳ* ክንፍ በሆነው የአል-ሸባብ አሸባሪ ቡድን መያዙን በስፍራው ያሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

የክስተቱ መንስዔ የቴክኒክ ብልሽት እንደሚሆን የታመነ ሲሆን ሄሊኮፕተሩ ያረፈው በጋልጋዱድ ክልል በአማጽያኑ ቁጥጥር ስር በምትገኘው ሂንዴሬ በተባለች አካባቢ ነው።

የአውሮፕላኑ ሠራተኞች እና ይዞት የነበረው ጭነት በአሸባሪዎቹ እጅ ውስጥ እንደሆኑ ተዘግቧል።

በሄሊኮፕተሩ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ቁጥር፣ የምዝገባ ቁጥሩ እና የጭነቱ ዓይነት እስካሁን አልታወቀም።

ስለ ክስተቱ እስካሁን ይፋዊ ማረጋገጫ አልተሰጠም።

ሄሊኮፕተሩ በበለድዌይን (ሂራን ክልል) እና በዊሲል (ሙዱግ ክልል) መካከል እየተጓዘ ነበር።

*አል-ቃይዳ በሩሲያ እና በሌሎች ሀገራት በአሸባሪነት የተፈረጀ የሽብር ድርጅት ነው፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0