'ህይወት በአብያተ መንግሥት' የተሰኘ መርኃ-ግብር በጎንደር ከተማ ተጀመረ
16:43 29.09.2025 (የተሻሻለ: 16:44 29.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
'ህይወት በአብያተ መንግሥት' የተሰኘ መርኃ-ግብር በጎንደር ከተማ ተጀመረ
በከተማዋ የሚገኘው የፋሲል አብያተ መንግሥትን የቱሪስት ተደራሽነት ለማሳደግ እንዲሁም የቀደምት ነገሥታት ክዋኔዎች እና ታሪካዊ ሁነቶች በትውልዱ እንዲዘከሩ ለማድረግ መጀመሩን የቱሪዝም ሚኒስተሯ ሰላማዊት ካሣ ተናግረዋል፡፡
‘ህይወት በአብያተ መንግሥት’ በቀደመው ጊዜ ነገሥታቱ ይከውኗቸው የነበሩ ሁነቶችን ከመመለስ ባለፈ ጎብኝዎችን የታሪክ አካል እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
መርኃ ግብሩ የቱሪስቶችን የቆይታ ግዜ ከማራዘም ባለፈ በቅርሶች ላይ ህይወትን ለመዝራት እንደሚያግዝ ያነሱት ሚኒስትሯ፤ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ባሉ አብያተ መንግሥታት እንደሚስፋፋም ጠቁመዋል፡፡
በማስጀመሪያ መርኃ-ግብሩ 300 ባለሙያዎች የተሳተፉበት የቀደምት ነገሥታት የጥንት ክዋኔዎች ቀርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


