በኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ዕጣ ፈንታ የሚወስን መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለፀ
15:44 29.09.2025 (የተሻሻለ: 15:54 29.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ዕጣ ፈንታ የሚወስን መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለፀ
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን በነዳጅ የሚሠሩና አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ተሽከርካሪዎች ዕጣ ፈንታቸው ወደ ኤሌክትሪክ መቀየር ነው ማለታቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ለዚህም የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ለመቀየር የሚያስችል ስታንዳርድ ፀድቆ መመሪያ በዝግጅት ሂደት ላይ ይገኛል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በመጪዎቹ 10 ዓመታት ወደ ሀገር ውስጥ ከሚገቡ ተሽከርካሪዎች መካከል 95 በመቶ የሚሆኑትን ኤሌክትሪክ ለማድረግ እየሠራች መሆኑን ሚኒስትር ዴታው ተናግረዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X