ማሌዥያ በአዲስ አበባ ኢምባሲዋን ዳግም ከፈተች
12:09 29.09.2025 (የተሻሻለ: 12:14 29.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ማሌዥያ በአዲስ አበባ ኢምባሲዋን ዳግም ከፈተች
ከ43 ዓመታት በኋላ ዳግም የተከፈተው የደቡብ እስያዋ ሀገር ኤምባሲ፤ ከመስከረም 13፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ መጀመሩን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
“የኤምባሲው ዳግም መከፈት ማሌዥያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የጠበቀ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት ያጎላል። ይህ ደግሞ በተለያዩ የጋራ ፍላጎት መስኮች፤ በተለይም በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት አዲስ የትብብር ዕድሎችን ለማሰስ እንደ ማነቃቂያ ሆኖ ያገለግላል” ሲል ሚኒስቴሩ ጠቅሷል፡፡
የኤምባሲው በአዲስ አበባ መከፈት ማሌዥያ ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ግንኙነቷን እንድታጠናክር ዕድሎችን እንደሚፈጥርላት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በመግለጫው ጠቁሟል።
ኤምባሲው በአሁኑ ወቅት በጊዜያዊነት ከሸራተን አዲስ ሆቴል ሥራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ማሌዥያ የኢትዮጵያ ኤምባሲዋን እ.ኤ.አ 1982 ነበር የዘጋችው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X