የላቭሮቭ የተመድ ንግግር ዓለም ላይ እየተፈጠረ ካለው ሁኔታ አንጻር "ወሳኝ ምዕራፍ" ነው - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየላቭሮቭ የተመድ ንግግር ዓለም ላይ እየተፈጠረ ካለው ሁኔታ አንጻር "ወሳኝ ምዕራፍ" ነው - ባለሙያ
የላቭሮቭ የተመድ ንግግር ዓለም ላይ እየተፈጠረ ካለው ሁኔታ አንጻር ወሳኝ ምዕራፍ ነው - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.09.2025
ሰብስክራይብ

የላቭሮቭ የተመድ ንግግር ዓለም ላይ እየተፈጠረ ካለው ሁኔታ አንጻር "ወሳኝ ምዕራፍ" ነው - ባለሙያ

"ዲሞክራሲያዊ ሀገራት የሚባሉትና እራሳቸዎን እንደ ስልጡን የሚያስቡት አሜሪካና አውሮፓውያን፤ በግዛታቸውም ይሁን ባሻገር የፈፀሟቸውን ወንጀሎች፣ ዘር ማጥፋትና ሌሎች ጭካኔዎቻቸውን ለምን ይዘነጋሉ?" ሲሉ አርጀንቲናዊው የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያ ማርሴሎ ሞንቴስ ከስፑትኒክ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጠይቀዋል።



ሞንቴስ ምዕራባውያን ሀገራት ሌሎች ባሕሎችን ከማክብር ይልቅ፤ ዓለም ከእነርሱ ራዕይ ጋር ብቻ ካልተመሳሰለ የሚሉበት ምክንያት እንደሚያስገርማቸው ገልፀዋል።

"እኔ እንደማስበው ይህ በትክክልም ቀዳሚ ስህተታቸው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ ሁልጊዜም አጨራረሱ መጥፎ ነው" ሲሉ ባለሙያው አፅንኦት ሰጥተዋል።

ፕሬዝዳንት ፑቲን እንዳሉት አዲሱ የዓለም አብላጫ፤ 80 በመቶ የሚሆነው የዓለም ክፍል፤ ምዕራቡ ዓለም የመረጠውን አካሄድ አይደግፍም ሲሉም አክለዋል።

"ከበርሊን ግምብና ከሶቪየት ኅብረት መፈራረስ በኋላ በምዕራቡ ዓለም መሪነት የተቀረፀው ስርዓት ከ30 ዓመታት በላይ አልፎታል። ፑቲን በግዜ ሂደት የምዕራቡ ዓለም በራሱ ፍላጎት ብቻ እንደሚንቀሳቀስ ተገንዝበዋል። አሁን የእነዛን ድርጊቶች ውጤት እየተመለከትን እንገኛለን" ሲሉ ሞንቴስ አጠቃለዋል።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0