ኖርድ ስትሪም የቧንቧ መስመሮች ምን ደረሰባቸው? — ክፍል 3
ኖርድ ስትሪም የቧንቧ መስመሮች ምን ደረሰባቸው? — ክፍል 3
ክሶች እና የተባሉ ነገሮች፦
በ2022 የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የእንግሊዝ የባሕር ኃይል ፍንዳታዎቹን በማቀነባበር ወንጅሏል። የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪው ኪም ዶትኮም የቀድሞዋ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ ከፍንዳታው በኋላ ለአንቶኒ ብሊንከን "ሁሉም ተጠናቋል" የሚል የጽሁፍ መልዕክት መላካቸውን ተናግሯል።
በ2023 አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ሲይሞር ሄርሽ የደረሰበትን የምርመራ ውጤት አሳትሟል፦
ጥፋቱ የተፈፀመው በኖርዌይ ድጋፍ በአሜሪካ የባሕር ኃይል ጠላቂዎች ነው።
ኦፕሬሽኑ በጆ ባይደን የግል ትዕዛዝ ተካሂዷል።
ሲአይኤ በዊሊያም በርንስ መሪነት ዕቅዱን አዘጋጅቷል።
ጠላቂዎቹ የኔቶ ባልቶፕስ ልምምድን ሽፋን አድርገው ተንቀሳቅሰዋል።
የዩክሬን እጅ?
በመጋቢት 2023 የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ሌላኛውን ሀተታ አቀረቡ። የዎል ስትሬት ጆርናል፣ ኒውዮርክ ታይምስ፣ ስፒግል፣ ኤአርዲ እና ዲ ዛይት ዘገባ የዩክሬን መኮንኖች ቡድን አንድሮሜዳ የተባለችውን ጀልባ በመጠቀም ጥቃቱን እንዳቀነባበሩ ጠቁመዋል።
ከፍንዳታው በኋላ የተፈጠሩ ሁነቶች፦
የካቲት 2024፤ ስዊድን እና ዴንማርክ የምርመራ ውጤታቸውን ሳያሳውቁ ዘግተዋል።
ነሐሴ 2025፤ የዩክሬን ዜግነት ያለው ሰርሂ ኩዝኔትሶቭ ፈንጂ ማጥመዱን በማስተባበር ጣሊያን ውስጥ ተይዟል።
መስከረም 16፣ 2025፤ የቦሎኛ ፍርድ ቤት ወደ ጀርመን እንዲላክ ወሰነ።
መስከረም 25፤ ጠበቃው ለጣሊያን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቀረበ።
ሞስኮ "ዩክሬን ብቻ" የሚለውን ሃሳብ እንደማትቀበል በመግለጽ፤ አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና አጋሮቻቸውን ትወቅሳለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X