ጦርነት እና ግጭት የተለመዱ፤ ሰላም ቅንጦት ሆኗል - የጊኒ ባለሥልጣን

ሰብስክራይብ

ጦርነት እና ግጭት የተለመዱ፤ ሰላም ቅንጦት ሆኗል - የጊኒ ባለሥልጣን

በአንድ ወቅት በተባበሩት መንግሥታት ያስቀመጥነው ተስፋ በስጋት ተተክቷል ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው አማራ ካማራ ተናግረዋል። አክለውም ዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ ተቋማት እየተዳከሙ ነው ብለዋል።

ካማራ ያነሷቸው ተጨማሪ ቁልፍ ነጥቦች፦

▪ በአሁኑ ወቅት ዓለም የትኛውንም አህጉር ሳታስቀር ብጥብጥ ውስጥ መሆኗ ግልጽ ነው።

▪ ጊኒ ከአርብ ጀምሮ የዜጎቿን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ እና አንድ የሚያደርግ ሕገ-መንግሥት አግኝታለች።

▪ ጊኒ የስታንዳርድ እና ፑርን የተረጋጋ ምልከታ ቢ ፕላስ (B+) በማግኘት በመጀመሪያው ሉዓላዊ ደረጃ ታሪካዊ ምዕራፍ አሳክታለች።

▪የሀገሪቱን ብሔራዊ እና የማዕድን ዘርፍ ሉዓላዊነት በማስቀደም ብሔራዊ የማዕድን ደንብን ጨምሮ ሕግና መመሪያን የጣሱ ተቋማትን ፍቃድ ሰርዛለች።

▪ጊኒ የሲማንዱ 2040 አጠቃላይ ፕሮግራምን እየተገበረች ነው። ይህም በአምስት ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች ላይ የተገነባ ነው፦

🟠 ግብርና፣ የምግብ ኢንስትሪ እና ንግድ፣

🟠 ትምህርት እና ባሕል፣

🟠 መሠረተ ልማት፣ ትራንስፖርትና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች፣

🟠 ኢኮኖሚ፣ ፋይናንስ እና ኢንሹራንስ፣

🟠 ጤና እና ደህንነት።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0