በአፍሪካ በርካታ ዕድሎች አሉ - የዓለም የኒውክሌር ማኅበር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአፍሪካ በርካታ ዕድሎች አሉ - የዓለም የኒውክሌር ማኅበር
በአፍሪካ በርካታ ዕድሎች አሉ - የዓለም የኒውክሌር ማኅበር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.09.2025
ሰብስክራይብ

በአፍሪካ በርካታ ዕድሎች አሉ - የዓለም የኒውክሌር ማኅበር

"ሰፊ ሀብት ያላቸው በርካታ የአፍሪካ ሀገራት አሉ። ያንን ሀብት በመፈለግ እና በማውጣት ላይ በርግጥም ኢንቨስት ልናደርግ ይገባል” ሲሉ የዓለም የኒውክሌር ኅብረት ዋና ዳይሬክተር ሳማ ቢልባኦ ሊዮን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ቢልባኦ የሩሲያ የኒውክሌር ኮርፖሬሽን ሮሳቶም ሀገራት የኒውክሌር ኢነርጂ አቅማቸውን መጠቀም እንዲችሉ ያደረገ “አስደናቂ የትብብር ታሪክ” እንዳለው አንስተዋል።

የዓለም የኒውክሌር ነዳጅ ምርትን አስመልክቶ የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሯ፤ በርካታ ሀገራት የዩራኒየም ምርትን በመፈለግና በማውጣት ተጨባጭ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።

ሩሲያ እ.ኤ.አ በ2030 የመጀመሪያውን ዝግ የሙሉ ዑደት የኒውክሌር ኃይል ስርዓት በቶምስክ ክልል ለመገንባት ማቀዷ ላይ ሀሳብ ሲሰጡ፤ የሩሲያን አቅም አረጋግጠዋል።

የሀገሪቱን የ40 እና 50 ዓመት ፈጣን ሪአክተሮች የማንቀሳቀስ ልምድ በመጥቀስ፤ "ሩሲያ እንደዚህ አይነት ተግባራትን ለመፈፀም እውቀትና ባለሙያዎች አሏት" ብለዋል።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0