ኢትዮጵያ "አንሶ አፍሪካ" የተሰኘ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ልሕቀት ማዕከል በይፋ ከፈተች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ "አንሶ አፍሪካ" የተሰኘ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ልሕቀት ማዕከል በይፋ ከፈተች
ኢትዮጵያ አንሶ አፍሪካ የተሰኘ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ልሕቀት ማዕከል በይፋ ከፈተች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.09.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ "አንሶ አፍሪካ" የተሰኘ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ልሕቀት ማዕከል በይፋ ከፈተች

በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነው ይህ ማዕከል በአምቦ ዩኒቨርሰቲ ተከፍቷል።

'አንሶ' በቻይና መንግሥት ድጋፍ የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግርን ለመፍጠር እንዲሁም ሳይንስና ፈጠራን ለማበረታታት የሚሠራ ማዕከል መሆኑን የሀገር ውስጥ ሚዲያ የትምህርት ሚኒስቴር ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ፤ የማዕከሉ እውን መሆን ኢትዮጵያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ልሕቀት ማዕከል ለመሆን የጀመረችውን ጉዞ ያፋጥናል ብለዋል።

ተቋሙ “በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት፣ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እንዲሁም በቂ የሰው ኃይል ለማፍራት ሰፊ ዕድል የሚሰጥ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ማዕከሉ በአህጉሪቱ የሚገኙ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ምሁራኖችና ኢንዱስትሪዎች በጋራ የሚሠሩበት መሆኑም ተገልጿል፡፡

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0