የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በተመድ 80ኛ ጉባዔ ላይ ካደረጓቸው ንግግሮች፦
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በተመድ 80ኛ ጉባዔ ላይ ካደረጓቸው ንግግሮች፦
🟠 ዛሬ ላይ የፍልስጤም መንግሥት ምስረታን በተመለከተ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውሳኔን ለመቅበር የሚደረግ ሙከራን በተግባር እየተጋፈጥን ነው።
🟠 ለፍልስጤም እውቅና በሚሰጥበት ወቅት ምንም ዓይነት ግዛት እንዳይቀር የሚደረጉ ሙከራዎችን ለመከላከል አስቸኳይ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው።
🟠 ሩሲያ ምዕራባውያን የፀጥታው ምክር ቤት ማዕቀቦችን በኢራን ላይ መልሶ እንዲጥል የሚያደርጉትን ሙከራ ተቀባይነት የሌለውና ሕገ-ወጥ አድርጋ ትቆጥረዋለች።
🟠 ሩሲያ የዩክሬን ግጭት መንስኤዎችን ለመፍታት ለድርድር ዝግጁ ነች።
🟠 የሩሲያ ደህንነት እና ቁልፍ ጥቅም በአስተማማኝ ሁኔታ መረጋገጥ አለበት።
🟠 በዩክሬን ግዛቶች የሩሲያውያን እና የሩሲያኛ ተናጋሪ ሕዝቦች መብት ሊመለስ ይገባል።
🟠 ሩሲያ የኔቶ አባል ሀገራትን ለማጥቃት እቅድ የላትም፣ ነገር ግን ለማንኛውም ጥቃት የማያወላዳ አፀፋዊ ምላሽ ትሰጣለች።
🟠 ሞስኮ በቀጣይ የሩሲያ እና አሜሪካ ውይይት የዩክሬን ጉዳይ መፍትሄ እንደሚያገኝ ተስፋ ታደርጋለች።
🟠 ፑቲን በ 'ኒው ስታርት' ስምምነት ስር ገደቦችን ለማስቀመጥ ያቀረቡት ሃሳብ፤ የጦር መሳሪያ እሽቅድምድምን ለማስቀረት አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራል።
🟠 ሩሲያ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት መሻሻልን ትደግፋለች፤ ማንም ላይ የተለየ ዘመቻ አታደርግም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X