የኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት የመቀላቀል ፍላጎት 30 ሀገራት ደገፉ
12:05 27.09.2025 (የተሻሻለ: 12:14 27.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት የመቀላቀል ፍላጎት 30 ሀገራት ደገፉ
በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በተካሄደው የዓለም አቀፉ ንግድ ድርጅት 6ኛ የሥራ ቡድን ስብሰባ ላይ ለተነሱ ከ200 በላይ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ መሰጠቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ አስታውቀዋል።
በ5ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ ከ19 አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ ድጋፍ መስጠታቸውን ያወሱት ሚኒስትሩ፤ በ6ኛው ዙር ድጋፋቸውን ያሳዩ ሀገራት ቁጥር ወደ 30 ማደጉን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄ ካቀረበች ከ20 ዓመታት በላይ ከፈጀ ሂደት በኋላ ለአባልነት መቃረቧን ጠቁመዋል።
"በቀጣይም ትጋትና ርብርባችንን አጠናክረን በመቀጠል የባለብዙ ወገንና የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድሮችን የምናከናውን ይሆናል" ሲሉም ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X