ሩሲያ የሱዳን የትጥቅ ግጭት በአስቸኳይ መቆም እንዳለበት አሳሰበች
11:34 27.09.2025 (የተሻሻለ: 11:44 27.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ የሱዳን የትጥቅ ግጭት በአስቸኳይ መቆም እንዳለበት አሳሰበች
ሰርጌ ላቭሮቭ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ኢድሪስ ጋር ከተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ማድረጋቸውን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ውይይቱ የንግድና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ማሳደግ ላይ ትኩረቱን ያደረገ እንደነበርም ተገልጿል።
ውይይታቸው ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ ለዘለቀው የሱዳን ወታደራዊ-ፖለቲካዊ ቀውስ ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቷል።
ሩሲያ የትጥቅ ግጭቱ በፍጥነት እንዲያበቃ እና ብሔራዊ እርቅን ታሳቢ በማድረግ የመልሶ ግንባታ ሂደትን መጀመር አስፈላጊ እንደሆነ አጽንዖት ሰጥታለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X