ኢትዮጵያ በዓለም ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ከተሰነዘረባቸው ሀገራት ግንባር ቀደሟ መሆኗ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በዓለም ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ከተሰነዘረባቸው ሀገራት ግንባር ቀደሟ መሆኗ ተገለፀ
ኢትዮጵያ በዓለም ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ከተሰነዘረባቸው ሀገራት ግንባር ቀደሟ መሆኗ ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.09.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በዓለም ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ከተሰነዘረባቸው ሀገራት ግንባር ቀደሟ መሆኗ ተገለፀ

እንደ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፖሊስ ተቋም (ኢንተርፖል) የአፍሪካ የሳይበር ስጋት ግምገማ የ2025 ሪፖርት መሠረት እ.አ.አ በ2024 ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛው ዒላማ የተደረገች ሀገር እንደነበረች ይፋ አድርጓል፡፡

ኢትዮጵያ ማልዌር በመለየት በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ ስትሆን ይህም የተጠናከረ የሳይበር መከላከያ እና የተቀናጁ ምላሽ ስልቶች ላይ አስቸኳይ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ያሳያል መባሉን የግል ሚዲያ ሪፖርቱን ጠቅሶ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ ተደጋጋሚና ውስብስብ የሳይበር ስጋት የተደቀነባቸው፦

🟠 ወሳኝ የመሠረተ ልማት አውታሮች፣

🟠 የመንግሥት ተቋማት፣

🟠 የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪዎች፣

🟠 ዋና ዋና የልማት ፕሮጀክቶች፡፡

እነዚህ ጥቃቶች የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ማስፋፋያ አካል የሆኑትን ሞባይል ባንኪንግ፣ ኢ-ኮሜርስ እና ኦንላይን የሕዝብ አገልግሎቶችን እየተጠቀሙ እነደሆነ ተገልጿል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0