ከአፍሪካ በነፍስ ወከፍ እጅግ ሀብታም ስለሆነችው ሲሼልስ አጠቃላይ ምርጫ ማወቅ ያለብዎት ነገር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከአፍሪካ በነፍስ ወከፍ እጅግ ሀብታም ስለሆነችው ሲሼልስ አጠቃላይ ምርጫ ማወቅ ያለብዎት ነገር
ከአፍሪካ በነፍስ ወከፍ እጅግ ሀብታም ስለሆነችው ሲሼልስ አጠቃላይ ምርጫ ማወቅ ያለብዎት ነገር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.09.2025
ሰብስክራይብ

ከአፍሪካ በነፍስ ወከፍ እጅግ ሀብታም ስለሆነችው ሲሼልስ አጠቃላይ ምርጫ ማወቅ ያለብዎት ነገር

ከ77 ሺህ በላይ የሲሼልስ ዜጎች ከመስከረም 25 እስከ 27 በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊና የሕግ አውጪ ምርጫ ድምጽ እየሰጡ ነው።

በርቀት ባሉ ደሴቶች የሚኖሩ ነዋሪዎችና አስፈላጊ ሠራተኞች ሐሙስ ዕለት ድምጽ መስጠት የጀመሩ ሲሆን ዋናው ድምጽ አሰጣጥ ቅዳሜ በሶስቱ ትላልቅ ደሴቶች ላይ ይካሄዳል።

8⃣ ስምንት ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች የሚፎካከሩ ሲሆን እየመሩ ያሉት፦

ዋቬል ራምካላዋን፦ የቀድሞ የአንግሊካን ቄስ እና የአሁን ፕሬዚዳንት፣ የሲሼልስ ዲሞክራሲያዊ ህብረት መሪ፣ ለሁለተኛ የሥልጣን ዘመን እየተወዳደሩ ነው።

ፓትሪክ ሄርሚኒ፦ የተቀናቃኙ የተባበሩት ሲሼልስ ፓርቲ መሪ፡፡

አንድ እጩ ሙሉ በሙሉ ለማሸነፍ ከ50 በመቶ በላይ ድምጽ ማግኘት አለበት፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ከፍተኛ ድምጽ ያገኙት ሁለቱ ወደ ለሁለተኛ ዙር ያልፋሉ።

መራጮች የብሔራዊ ምክር ቤት አባላትንም እየመረጡ ሲሆን 26ቱ በቀጥታ የተመረጡ ተወካዮች እና እስከ 9 ያህሉ ደግሞ በምርጫ ክልል በተመጣጣኝ ውክልና የሚመረጡ ይሆናል። ተመራጩ ፕሬዝዳንትና ምክር ቤቱ ሁለቱም ለአምስት ዓመት ያገለግላሉ።

ዋና ዋና ነጥቦች፦

◻ ሲሼልስ በህንድ ውቅያኖስ የምትገኝ የ115 ደሴቶች ስብስብ ስትሆን፤ ወደ 120 ሺህ የሚጠጋ ሕዝብ አላት፡፡ ከዚህ ውስጥ ሦስት አራተኛው የሚኖረው በማሄ ዋና ደሴት ላይ ነው።

◻ በአፍሪካ በነፍስ ወከፍ እጅግ ሀብታም ሀገር ስትሆን፤ በቱሪዝምና በአሳ ማስገር የምትመራ ናት፡፡ ነገር ግን የኑሮ ውድነት፣ የአየር ንብረት አደጋዎች እና የሕዝቧን 10 በመቶ ያህል የሚያጠቃ ከባድ የሄሮይን ቀውስ ገጥሟታል።

◻ ሲሼልስ በ1976 ከነጻነት በኋላ ከአንድ ፓርቲ አገዛዝ ወደ ብዝሃ ፓርቲ ዲሞክራሲ በ1993 ተሸጋግራለች። የተባበሩት ሲሼልስ ፓርቲ ራምካላዋን እ.አ.አ በ2020 ድል ሥልጣኑን እስኪረከቡ ድረስ የበላይነት ነበረው።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0