የሩሲያ ግዙፍ የኢ-ኮሜርስ ኩባንያ በኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ዘርፍ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት አሳየ
19:35 26.09.2025 (የተሻሻለ: 19:44 26.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ግዙፍ የኢ-ኮሜርስ ኩባንያ በኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ዘርፍ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት አሳየ
አርደብሊውቢ በኢትዮጵያ ሎጂስቲክስ እና ዲጂታል ንግድ መሠረተ ልማት ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየቱን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የአርደብሊውቢ ልዑካን ቡድን ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ ጋር በነበረው ቆይታ በዲጂታል ንግድ፣ በሎጂስቲክስ እና በማስታወቂያ ያለውን ዓለም አቀፍ ልምድ ያቀረበ ሲሆን ዘመናዊ የመጋዘን መሠረተ ልማቶችን እና የኤሌክትሮኒክስ ሎጂስቲክስ ስርዓቶችን በማልማት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት ማቀዱን አመላክቷል።
ሚኒስትር ዴኤታው ደንጌ ቦሩ ይህንን እንቅስቃሴ በአዎንታ እንደሚቀበሉት በመግለፅ፤ ያልዳበረ የኢ-ኮሜርስ ሎጂስቲክስ እና የዲጂታል ንግድ መሠረተ ልማትን የማሳደግ አስቸኳይ ፍላጎት መኖሩን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሁለቱ ወገኖች የኢትዮጵያን ሎጂስቲክስ እና የኢ-ኮሜርስ ሥነ-ምህዳር ለማጠናከር ተጨማሪ የቴክኒክ ውይይቶችን እና አስቻይ የኢንቨስትመንት ማዕቀፎችን ለመመልከት ተስማምተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X