ኖርዶ ስትሪም - Sputnik አፍሪካ

በኖርድ ስትሪም ቧንቧዎች ላይ የተፈፀሙ የሽብር ጥቃቶች

ኖርድ ስትሪም (1224 ኪ.ሜ) እና ኖርድ ስትሪም 2 (1200 ኪ.ሜ.) በባልቲክ ባህር ስር የሚሄዱ እና የጋዝ አቅርቦቶች የመተላለፊያ ሀገራትን በማለፍ ከሩሲያ ወደ አውሮፓ ጋዝ እንዲተላለፍ የሚያስችሉ ቧንቧዎች ናቸው።

• እያንዳንዱ የቧንቧ መስመር በዓመት 55 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ጋዝ የመያዝ አቅም ያላቸው ሁለት መገናኛዎች አሉት። የሁለቱም የቧንቧ መስመሮች አጠቃላይ የዲዛይን አቅም 110 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ነው።
• አጠቃላይ የፕሮጀክት ኢንቨስትመንት፡ 7.4 ቢሊዮን ዩሮ።
ኖርዶ ስትሪም የጋዝ መስመሮች ኢንፎግራፊክ - Sputnik አፍሪካ
ኖርዶ ስትሪም የጋዝ መስመሮች ኢንፎግራፊክ
የቧንቧ መስመር ግንባታው ታሪክ
• ኖርድ ስትሪም፡ ግንባታ የጀመረው በ2010 ሲሆን ከ2012 ጀምሮ የንግድ አቅርቦቶች ተጀምረዋል። ከ10 ዓመታት በላይ ለአውሮፓ አስተማማኝ የጋዝ አቅርቦቶችን አቅርቧል። ጋዝፕሮም ብልሽቶችን በመለየቱ በነሐሴ 2022 መጨረሻ ላይ አቅርቦት ቆሟል። የጀርመን ኩባንያ ሲመንስ ጉዳቱን ለመጠገን ዝግጁ ቢሆንም በምዕራባውያን ማዕቀቦች ምክንያት የማይቻል ሆኗል፡፡
• ኖርድ ስትሪም 2፡ መስከረም 2021 ተጠናቆ በጋዝ ቢሞላም ጀርመን የእውቅና ማረጋገጫ በማገዷ ምክንያት ሳይጀመር ቀርቷል፡፡
ኖርዶ ስትሪም 2 - Sputnik አፍሪካ
ኖርዶ ስትሪም 2
የቧንቧ ዝርጋታ መርከብ ፎርቱና ከዊስማር ወደብ ስትወጣ  - Sputnik አፍሪካ
የቧንቧ ዝርጋታ መርከብ ፎርቱና ከዊስማር ወደብ ስትወጣ
ሰራተኞች በሩሲያ፣ ሌኒንግራድ ክልል፣ ኪንጊሴፕ ከተማ ውጭ በሚገኘው የኖርዶ ስትሪም 2 የጋዝ መስመር ግንባታ ቦታ ላይ እየሰሩ። የኖርዶ ስትሪም 2 ፕሮጀክት ወደ 55 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር (ወደ 2 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ የሚጠጋ) ጋዝ በቀጥታ ወደ ጀርመን እና ሌሎች የአውሮፓ አገሮች የሚያደርስ መንትያ የጋዝ መስመር ግንባታን ያካትታል - Sputnik አፍሪካ
ሰራተኞች በሩሲያ፣ ሌኒንግራድ ክልል፣ ኪንጊሴፕ ከተማ ውጭ በሚገኘው የኖርዶ ስትሪም 2 የጋዝ መስመር ግንባታ ቦታ ላይ እየሰሩ። የኖርዶ ስትሪም 2 ፕሮጀክት ወደ 55 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር (ወደ 2 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ የሚጠጋ) ጋዝ በቀጥታ ወደ ጀርመን እና ሌሎች የአውሮፓ አገሮች የሚያደርስ መንትያ የጋዝ መስመር ግንባታን ያካትታል
1.
ኖርዶ ስትሪም 2
2.
የቧንቧ ዝርጋታ መርከብ ፎርቱና ከዊስማር ወደብ ስትወጣ
3.
ሰራተኞች በሩሲያ፣ ሌኒንግራድ ክልል፣ ኪንጊሴፕ ከተማ ውጭ በሚገኘው የኖርዶ ስትሪም 2 የጋዝ መስመር ግንባታ ቦታ ላይ እየሰሩ። የኖርዶ ስትሪም 2 ፕሮጀክት ወደ 55 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር (ወደ 2 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ የሚጠጋ) ጋዝ በቀጥታ ወደ ጀርመን እና ሌሎች የአውሮፓ አገሮች የሚያደርስ መንትያ የጋዝ መስመር ግንባታን ያካትታል
የምዕራብ የኖርድ ስትሪም ተቃውሞ
• እ.ኤ.አ በ2018 የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን የኖርድ ስትሪም 2 ፕሮጀክት የአውሮፓን የኢነርጂ ደህንነት ይጎዳል በማለት ተቃውመውታል፡፡ ሞስኮ ኃይልን እንደ ፖለቲካ መሳሪያ ትጠቀምበታለች ብለው ያምናሉ። እንደ ቲለርሰን ገለጻ ዩናይትድ ስቴትስ የአሜሪካን ፈሳሽ ጋዝ በማቅረብ ለአውሮፓ (በተለይ ፖላንድን) የሃይል ምንጮችን በማስፋት ትረዳለች።
• እ.ኤ.አ በ2022 ፍንዳታው ከመከሰቱ በፊት ጆ ባይደን የሩሲያ “ታንኮች ወይም ወታደሮች የዩክሬንን ድንበር የሚያቋርጡ” ከሆነ የማስተላለፊያውን ሥራ እንደሚያግዱ ዝተዋል። አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ሲይሞር ሄርሽ እንደዘገበው ባይደን የቧንቧ መስመሮችን ፑቲን የተፈጥሮ ጋዝን መሳሪያ አድርገው ሊጠቀሙበት ይችላልሉ ብለው ያምናሉ፡፡
• ዶናልድ ትራምፕ እ.ኤ.አ በ2019 በኖርድ ስትሪም ላይ ማዕቀብ መጣል ብቻ ሳይሆን ባይደን ወደ አውሮፓ የሚወስደውን የሩሲያ የቧንቧ መስመር አጽድቀዋል በማለት ከሰዋል። እ.ኤ.አ በ2024 ከአሜሪካዊው ጋዜጠኛ ተከር ካርልሰን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ትራምፕ የቧንቧ መስመሩን በዋነኝነት ያወደሙት እርሳቸው መሆናቸውን አስታውሰዋል።
• ከዩናትድ ስቴጽ በተቃራኒ በአንጌላ ሜርክል የሚመራው የጀርመን መንግሥት ፕሮጀክቱን ደግፎ ነበር።
በኖርዶ ስትሪም 2 የጋዝ መስመር ግንባታ ቦታ ላይ የሰራተኛ የደንነት ቆብ (ኮፍያ) - Sputnik አፍሪካ
በኖርዶ ስትሪም 2 የጋዝ መስመር ግንባታ ቦታ ላይ የሰራተኛ የደንነት ቆብ (ኮፍያ)
አቅጣጫ ማስቀየሪያዎች፡ በ2022 ምን ተፈጠረ
• እ.ኤ.አ በመስከረም 26፣ 2022 ከኖርድ ስትሪም እና ኖርድ ስትሪም 2 ቧንቧዎች መካከል ሦስቱ በባልቲክ ባሕር ውስጥ በ80 ሜትሮች ጥልቀት ላይ ፈንድተው አራት የጋዝ ፍሳሾች ተገኝተዋል።
• ክስተቱ የተከሰተው በዴንማርክ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ነው። የስዊድን የመሬት መንቀጥቀጥ ተመራማሪዎች በቧንቧ መስመሩ ላይ ሁለት ፍንዳታዎችን መዝግበዋል፡፡
• በዴንማርክ፣ በስዊድን እና በጀርመን ያሉ ባለሥልጣናት አቅጣጫ ማስቀየርን ከጨዋታ ውቺ አላደረጉም። ፍንዳታዎቹ ለአስርት ዓመታት በተመጣጣኝ ዋጋ የሩሲያ ጋዝ ወደ ጀርመን እና ሌሎች የምዕራብ አውሮፓ ሀገራት ሲያደርሱ በነበሩ መሰረተ ልማቶች ላይ ታይቶ የማይታወቅ ውድመት አስከትሏል።
• በመስከረም 28፣ የሩሲያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በዓለም አቀፍ የሽብርተኝነት ድርጊት ላይ ክስ ከፍቷል፡፡
• በመስከረም 30፣ ቭላድሚር ፑቲን ፍንዳታው "የአውሮፓን የኢነርጂ መሠረተ ልማት ለማጥፋት" ዓላማ እንዳለው ተናግረዋል.
• የሽብር ጥቃቱን የፈፀሙት ተለይተው አልታወቁም።
ኖርዶ ስትሪም የህቡዕ ጥፋት ኢንፎግራፊክ - Sputnik አፍሪካ
ኖርዶ ስትሪም የህቡዕ ጥፋት ኢንፎግራፊክ
የሽብር ጥቃት ምርመራ - ይፋዊ መግለጫዎች እና የምዕባዊያን ሚዲያ አውድ
• ጀርመን፣ ዴንማርክ እና ስዊድን እ.አ.አ በጥቅምት ወር 2022 ሩሲያን ያገለለ ብሔራዊ ምርመራ ጀመሩ። ቦታው ላይ የፈንጂዎች ምልክት አግኘቶ የነበረው የስዊድን የጸጥታ አገልግሎት ፤ ፍንዳታው የታሰበበት እንደነበር አረጋግጧል።
• ሞስኮ ሩሲያን ያካተተ ዓለም አቀፍ ምርመራ እንዲደረግ እና ቁሳቁሶቹን ለማግኘት ደጋግማ ጠይቃለች። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ለሁኔታው የማጭበርበር እና የማወናበድ ስያሜ ሰጥቶት ነበር።

እ.አ.አ በጥቅምት ወር 2022 "ኤክስፕረስን" የተሰኘው የስዊድን ጋዜጣ በኖርድ የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚያሳይ የመጀመሪያውን ምስል ለህትመት አበቃ። የውኃ ውስጥ ሰው አልባ ተሽከርካሪ በማስተላለፊያ መስመሩ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

የመጀመሪያው የ "ኖርዶ ስትሪም" የጋዝ ቧንቧ መስመር ጉዳት የመጀመሪያ ምስሎች
• እ.አእ.አ.አ ጥቅምት 31/2022 የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋዝፕሮም የተሰኘው የሩሲያ የሃይል ኩባንያ የኖርድ የጋዝ ማስተላለፊያ መስመሮች የፍንዳታ ቦታን ለመመርመር ፈቃድ ማግኘቱን አስታውቀዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻ ፍንዳታው በተፈጸመበት ቦታ ላይ ሁለት ጉድጓዶች ተፈጥረዋል። 40 ሜትር ገደማ የሚሆነው የማስተላለፊያው መስመር የተቀደደ እና 90 ዲግሪ የታጠፈ ነው። የፍንዳታው ፍንጣቂ በአቅራቢያ የሚገኘውን የኖርድ መስመር ቁጥር ሁለትን ሳያወድም አለመቅረቱንም ሐሳብ ሰንዝሯል።
• የቧንቧ መስመሩን በማፈንዳት ዝግጅት እና ማስፈጸም ላይ የብሪታንያ የባህር ኃይል ተወካዮች በዩክሬን ኒኮላይቭ ክልል ኦቻኮቭ ከተማ ተሳትፎ ማድረጋቸውን እ.አ.አ በጥቅምት ወር 2022 የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል። የሜጋአፕሎድ ካምፓኒ መስራች የሆነው ታዋቂው የጀርመን እና ፊንላንድ ጥምር ዜግነት ባለቤት ኪም ዶትኮም ፤ የቀድሞ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ ከፍንዳታው በኃላ ለቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን "ሁሉም ተከናውኗል" በማለት የጽሑፍ መልዕክት ልከዋል ሲል ተናግሯል። የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፀሐፊ ኒኮላይ ፓትሩሼቭ ይህ ጽሑፍ "በፍንዳታው ውስጥ የብሪታንያ የባህር ኃይል ተሳትፎን ያረጋግጣል" ብለዋል። የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት ኃላፊ የሆኑት ሰርጌይ ናሪሽኪን በተጨማሪም ሩሲያ ይህ መልዕክት በኖርድ የጋዝ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የተከሰተውን ፍንዳታ እንደሚያመለክት ለማመን ሌሎች የእጅ አዙር ምክንያቶች እንዳላትም ጠቅሰዋል።
የጋዝ ፍሰሻ ቦታ በኖርዶ ስትሪም 2 ላይ። እ.ኤ.አ በመስከረም 26 ቀን ኖርዶ ስትሪም 2 ኤጂ (Nord Stream 2 AG) በዴንማርክ የባህር ክልል ውስጥ ከቦርንሆልም ደሴት አቅራቢያ በሚገኝ የኖርዶ ስትሪም የጋዝ ቧንቧ መስመር 2 ላይ ድንገተኛ አደጋ እንደደረሰበት ሪፖርት ተደርጓል፣ ይህም ከከፍተኛ የግፊት ቅናሽ ጋር ተያይዞ ነበር። ለአርትዖት አገልግሎት ብቻ። በማህደር የማይቀመጥ ለንግድ መጠቀም ወይም ለማስታወቂያ ዘመቻዎች መጠቀም አይፈቀድም - Sputnik አፍሪካ
የጋዝ ፍሰሻ ቦታ በኖርዶ ስትሪም 2 ላይ። እ.ኤ.አ በመስከረም 26 ቀን ኖርዶ ስትሪም 2 ኤጂ (Nord Stream 2 AG) በዴንማርክ የባህር ክልል ውስጥ ከቦርንሆልም ደሴት አቅራቢያ በሚገኝ የኖርዶ ስትሪም የጋዝ ቧንቧ መስመር 2 ላይ ድንገተኛ አደጋ እንደደረሰበት ሪፖርት ተደርጓል፣ ይህም ከከፍተኛ የግፊት ቅናሽ ጋር ተያይዞ ነበር። ለአርትዖት አገልግሎት ብቻ። በማህደር የማይቀመጥ ለንግድ መጠቀም ወይም ለማስታወቂያ ዘመቻዎች መጠቀም አይፈቀድም
በዚህ በስዊድን የባህር ዳርቻ ጥበቃ በተሰጠው ሥዕል ላይ፣ በባልቲክ ባህር ውስጥ ከኖርዶ ስትሪም የተከሰተው የጋዝ ፍሰት ከባህር ዳርቻ ጥበቃ አውሮፕላን የተነሳ ምስል ፣  ዕለተ ረብዑ ፣ መስከረም 27 ፣ 2022 እ.ኤ.አ - Sputnik አፍሪካ
በዚህ በስዊድን የባህር ዳርቻ ጥበቃ በተሰጠው ሥዕል ላይ፣ በባልቲክ ባህር ውስጥ ከኖርዶ ስትሪም የተከሰተው የጋዝ ፍሰት ከባህር ዳርቻ ጥበቃ አውሮፕላን የተነሳ ምስል ፣ ዕለተ ረብዑ ፣ መስከረም 27 ፣ 2022 እ.ኤ.አ
በዚህ በስዊድን የባህር ዳርቻ ጥበቃ የቀረበው ምስል ላይ፣  ከኖርዶ ስትሪም 2 አነስተኛ የሆነ ፍሰት ይታያል ፣ ዕለተ ረብዑ ፣ መስከረም 28፣ 2022 እ.ኤ.አ - Sputnik አፍሪካ
በዚህ በስዊድን የባህር ዳርቻ ጥበቃ የቀረበው ምስል ላይ፣ ከኖርዶ ስትሪም 2 አነስተኛ የሆነ ፍሰት ይታያል ፣ ዕለተ ረብዑ ፣ መስከረም 28፣ 2022 እ.ኤ.አ
1.
የጋዝ ፍሰሻ ቦታ በኖርዶ ስትሪም 2 ላይ። እ.ኤ.አ በመስከረም 26 ቀን ኖርዶ ስትሪም 2 ኤጂ (Nord Stream 2 AG) በዴንማርክ የባህር ክልል ውስጥ ከቦርንሆልም ደሴት አቅራቢያ በሚገኝ የኖርዶ ስትሪም የጋዝ ቧንቧ መስመር 2 ላይ ድንገተኛ አደጋ እንደደረሰበት ሪፖርት ተደርጓል፣ ይህም ከከፍተኛ የግፊት ቅናሽ ጋር ተያይዞ ነበር። ለአርትዖት አገልግሎት ብቻ። በማህደር የማይቀመጥ ለንግድ መጠቀም ወይም ለማስታወቂያ ዘመቻዎች መጠቀም አይፈቀድም
2.
በዚህ በስዊድን የባህር ዳርቻ ጥበቃ በተሰጠው ሥዕል ላይ፣ በባልቲክ ባህር ውስጥ ከኖርዶ ስትሪም የተከሰተው የጋዝ ፍሰት ከባህር ዳርቻ ጥበቃ አውሮፕላን የተነሳ ምስል ፣ ዕለተ ረብዑ ፣ መስከረም 27 ፣ 2022 እ.ኤ.አ
3.
በዚህ በስዊድን የባህር ዳርቻ ጥበቃ የቀረበው ምስል ላይ፣ ከኖርዶ ስትሪም 2 አነስተኛ የሆነ ፍሰት ይታያል ፣ ዕለተ ረብዑ ፣ መስከረም 28፣ 2022 እ.ኤ.አ
• አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ሲይሞር ሄርሽ እ.ኤ.አ በ2023 ምርመራው ፣ ፍንዳታው በአሜሪካ የባህር ኃይል ኦፕሬሽን የተፈጸመ እና በኖርዌይ የተደገፈው ጥቃቱ ፤ በቀጥታ በጆ ባይደን ፈቃድ ተሰጥቶበት በቀድሞ የሲአይኤ ዳይሬክተር ዊልያም በርንስ የተግባር ዕቅድ የተነደፈለት ነው ይላል። እንደ ሄርሽ ገለጻ ውድመቱ የተፈጸመው የባህር ሃይል የጋራ ልምምድን ሽፋን ባደረጉ ጠላቂዎች ነው። የአሜሪካ እና የኖርዌይ ባለስልጣናት እነዚህን ክሶች ስሜት የማይሰጡ በማለት ውድቅ አድርገዋቸዋል።
• ጥቃቱ በዩክሬን መኮንኖች ቡድን የተቀባበረ መሆኑን ኒዮርክ ታይምስን ጨምሮ የጀርመን ጋዜጦች እና የቴሌቭዥን ማሰራጫዎች ( ስፒግል፣ ኤአርዲ እና ዳይ ዚት) ዘግበዋል። ለኦፕሬሽኑም የአንድሮሜዳ ጀልባ ጥቅም ላይ መዋሉም ተጠቁሟል። የዩክሬን የጦር ሃይሎች አዛዥ ቫለሪይ ዛሉዥኒ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዘዋወሩ ፈቃድ ሰጥተው እንደነበር የገለፁ ሲሆን ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ግን አልተነገረም ተብሏል።
• በየካቲት 2024፣ ስዊድን እና ዴንማርክ የህዝብ ውጤቶችን ሳያሳዩ ምርመራቸውን ዘግተዋል።
• እ.ኤ.አ በነሐሴ 2025፣ የዩክሬን ዜግነት ያለው ሰርጌይ ኩዝኔትሶቭ በጣሊያን በቁጥጥር ስር ዋለ። የጀርመን አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ፈንጂዎቹን ያስቀመጠውን ቡድን አስተባባሪ አድርጎ ይመለከተዋል።
• እ.ኤ.አ በመስከረም 16 ፣ 2025፣ የቦሎኛ ፍርድ ቤት (ጣሊያን) ኩዝኔትሶቭን ለጀርመን ባለስልጣናት አሳልፎ እንዲሰጥ ወሰነ። በመስከረም 25፣ ጠበቃው አሳልፎ የመስጠት ውሳኔውን ለጣሊያን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠየቀ።
• ሩሲያ በኖርዶች ስትሪምስ ላይ ለደረሰው ፍንዳታ የዩክሬን ግንኙነት ብቻ የሚለው አመክኞ ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጽ፣ ፍንዳታዎቹን በቀጥታ አሜሪካን እና አጋሮቿን፣ እንግሊዝን ጨምሮ ተሳትፈውበታል ትላለችትወቅሳለች።
• ጀርመን ምርመራዋን አሁንም እንደቀጠለች ነው።
የፑቲን ንግግር ከጥቃቶቹ ኋላ ማን እንደነበረ
ቭላድሚር ፑቲን እ.ኤ.አ. እ.ኤ.አ በ የካቲት ፣ 2024 ከታከር ካርልሰን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የኖርድ ስትሪም የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመርን ማን እንዳፈነዳ ገለጹ።
ታከር ካርልሰን፡ "ኖርድ ስትሪምን ማን አፈነዳው?"
ቭላድሚር ፑቲን፡ "እርስዎ ነዎት፣ በእርግጠኝነት" (ሳቅ)።
ታከር ካርልሰን፡ "በዚያ ቀን ስራ በዝቶብኝ ነበር። ኖርድ ስትሪምን አላፈነዳሁም። ቢሆንም አመሰግናለሁ።"
ቭላድሚር ፑቲን፡ "እርስዎ በግልዎ ሌላ ቦታ ሊሆኑ ቢችሉም ፣ ‘ሲአይኤ’ ግን በወቅቱ ሌላ ቦታ ነበርኩ ሊል አይችልም።"
ቭላድሚር ፑቲን ከታከር ካርልሰን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ የኖርዶ ስትሪም የነዳጅ ቧንቧ መስመርን ማን እንደፈነዳ ሲያስረዱ
Go back to the beginningGo back to the main page
አዳዲስ ዜናዎች
0