የኃይል ምንጮችን ለማብዛትና አስተማማኝ ለማድረግ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ወሳኝ ነው - የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኢነርጂ ሶሳይቲ
18:12 26.09.2025 (የተሻሻለ: 18:14 26.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኃይል ምንጮችን ለማብዛትና አስተማማኝ ለማድረግ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ወሳኝ ነው - የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኢነርጂ ሶሳይቲ
በውሃ ላይ ከተመሠረተ የኃይል አማራጭ ባሻገር በመመልከት ቅይጥ ምንጮችን መጠቀም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኢነርጂ ሶሳይቲ ፕሬዝዳንት እምሻው ዳምጠው (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
“ኢትዮጵያ ለሰላማዊ ዓላማ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫን ለመገንባት የጀመረችው ውጥን የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ልማት ለማረጋገጥና የተረጋጋ የኃይል ምንጭ ለማግኘት ያስችላታል” ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እንደ ኒውክሌር ላሉ ሌሎች የኃይል ምንጮች መነሻ በመሆን ወሳኝ ሚና ይጫወታልም ብለዋል ዶ/ር እምሻው።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኢነርጂ ሶሳይቲን ከማቋቋም ጀምሮ ሚና ከነበረው የሩሲያው ሮሳቶም ኩባንያ ጋር በትብብር እየሠሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና የሩሲያ ሮሳቶም ኩባንያ በኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ዙሪያ፤ በሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፊት ትናንት ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X