የባሕል ሙዚቃ ለአገር ገጽታ ግንባታ ያለውን ዕምቅ አቅም ይበልጥ መጠቀም ይገባል - ተወዳጁ የዋሽንት ተጫዋች

ሰብስክራይብ

የባሕል ሙዚቃ ለአገር ገጽታ ግንባታ ያለውን ዕምቅ አቅም ይበልጥ መጠቀም ይገባል - ተወዳጁ የዋሽንት ተጫዋች

የመሶብ የባሕል ሙዚቃ ባንድ መሥራች ጣሰው ወንድም፤ የኢትዮጵያን የባሕል ሙዚቃ ለተቀረው የዓለም ሕዝብ ጆሮ ተስማሚ አድርጎ በማቅረብ፤ የሀገሪቱን ባሕል፣ ታሪክ እና ማንነት በስፋት ለማስተዋወቅ ከጓደኞቹ ጋር እየሠራ መሆኑን ይገልጻል።

"የእኛን ባሕላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች ከሌሎች ሀገራት የሙዚቃ መሣሪያዎች ጋር በማዋሐድ ከበርካታ ሀገራት ጋር ሠርተናል። ተቀላቅለን ስለምንጫወት ሙዚቃው እና ጭፈራው ልዩ ሕብር ይኖረዋል። ሙዚቃ ይበልጥ አቅም የሚኖረውም በዚህ መንገድ ነው" ብሏል።

የዋሽንት ተጫዋቹ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበረው ቆይታ ወጣቶች የኢትዮጵያን ባሕላዊ የመዚቃ መሣሪያዎች ተምረው እንደ ሙያ ለመያዝ ያላቸው ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0