የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወደ ተሟላ ኦንላይን ግብይት መግባቱን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወደ ተሟላ ኦንላይን ግብይት መግባቱን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወደ ተሟላ ኦንላይን ግብይት መግባቱን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.09.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወደ ተሟላ ኦንላይን ግብይት መግባቱን አስታወቀ

ባለፈው በጀት ዓመት የቀጥታ የበይነ መረብ ግብይት ስርዓት በመተግበር ነጋዴዎች ባሉብት ሆነው እንዲገበያዩ ሲሠራ የቆየው ምርት ገበያው፤ በዘንድሮው ዓመት የኦንላይን ግብይትን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሥራ አስፈፃሚ አቶ መርጊያ ባይሳ ተናግረዋል።

የግብይት ሥርዓቱ መተግበር ከጀመረበት ከሚያዚያ ወር ጀምሮ 12.5 ቢሊዮን ብር ዋጋ የሚተመን 127 ሺህ 830 ሜትሪክ ቶን ምርት ማገበያየት መቻሉን ጠቁመዋል።

የግብርና ምርቶች ግብይት ሥርዓትን በማዘመን፣ ግልፀኝነትንና መተማመንን በመፍጠር በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ስርዓት ውስጥ ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም አስረድተዋል።

የኦንላይን የግብይት ሥርዓቱ ምቹ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋ፣ ከሰው ንክኪ ነፃ የሆነና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0