የኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የቻይና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ የሁለትዮሽ የትብብር ስብሰባ አካሄዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የቻይና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ የሁለትዮሽ የትብብር ስብሰባ አካሄዱ
የኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የቻይና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ የሁለትዮሽ የትብብር ስብሰባ አካሄዱ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.09.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የቻይና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ የሁለትዮሽ የትብብር ስብሰባ አካሄዱ

በውይይቱ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ እና ቻይና ከ1970ዎቹ ጀምሮ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምርምርና በተለያዩ ዘርፎች አጋርነታቸውን እያሰፉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ባለፉት አስርት ዓመታት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ጠንካራ ትብብር ዘርፈ ብዙ መሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ትብብሩን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ቁርጠኛ እንደሆነች ተናግረዋል።

የቻይናው ሚኒስትር ዪን ሄጁን በበኩላቸው የሁለቱ ሀገራት አጋርነት በብሪክስ ማዕቀፍ እና በቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ በኩል እየተጠናከረ ነው ብለዋል።

"ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በቴክኖሎጂ እና በሳይንስ መስክ ለመተባበር እና የሁለቱን ሀገራት የጋራ ምርምር እና ልማት ለማበረታታት ፈቃደኛ ናት" ሲሉ አክለዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0