በሱዳን የውጭ ቅጥረኞች በተሠማሩበት "ታይቶ የማይታወቅ ጦርነት" ዓለም አቀፍ ሕግ እያፈረሰ ነው ሲሉ የሀገሩቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ተናገሩ
በሱዳን የውጭ ቅጥረኞች በተሠማሩበት "ታይቶ የማይታወቅ ጦርነት" ዓለም አቀፍ ሕግ እያፈረሰ ነው ሲሉ የሀገሩቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ተናገሩ
በ80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ፕሮፌሰር ካሚል ኤል-ታይብ ኢድሪስ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች፦
◻ "ሱዳን ደምታለች"፣ "ከዚህ በፊት ያልታየ ጦርነት" እና "ወረራ" ገጥሟታል፣ መንደሮቿና ከተሞቿ ፀጥታ ሰፍኖባቸዋል።
◻ በጦርነቱ ውድመት መካከል፣ "ሞት አሻፈረኝ" ያሉ ስደተኞች፣ ገበሬዎች እና እናቶች አሁንም አሉ።
◻ በሱዳን ዓለም አቀፍ የሕግ መርሆዎች እየተሸረሸሩ እና "የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ብሎም የውጭ ቅጥረኞች ስምሪት" እየተፈጸሙ በመሆናቸው የባለብዙ ወገን ትብብር "ከፍተኛ አደጋ" ውስጥ እንደሚገኝ አስጠንቅቀዋል።
◻ ወታደራዊ የፈጥኖ ደራሽ ኃይል አማፂ ቡድን ለሶስት ዓመታት ያህል ሀብትን ለመዝረፍ እና የሕዝብ ስብጥር ለውጥ ለማምጣት በማሰብ "የህልውና አደጋ" ፈፅሟል ሲሉ ከሰዋል፡፡
◻ ጠንካራ ብሔራዊ ተቋማት እንዲኖሩ፣ ለሚሊሻዎች የሚጓዘው የጦር መሳሪያ አቅርቦት እንዲቆም እና በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ጥሪ አቅርበዋል።
◻ የምክር ቤቱ የውሳኔ ቁጥር አዋጅ 1591 (2005) ላይ የሚፈፀሙ ጥሰቶች ፤ ጦርነቱን እና የሲቪሎችን ስቃይ በማራዘም ሰላምን ያደናቅፋሉ።
◻ ሰላም ለማምጣት ከውጭ ጣልቃ ገብነት፣ ከችኮላ መፍትሄዎች ወይም ለጽንፈኝነት ከሚሰጥ ድጋፍ ነጻ የሆነ የሱዳናውያን የፖለቲካ እና የማኅበራዊ ተሳትፎ ያስፈልጋል።
◻ የተኩስ አቁም፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መውጣት እና በአል ፋሸር ላይ የተጣለውን እገዳ ማንሳትን ጨምሮ ለብሔራዊ ፍኖተ ካርታ ድጋፋቸውን አረጋግጠዋል፤ የውሳኔ ቁጥር 2736 (2024) አፈጻጸም መዘግየቱን ተችተዋል።
◻ በሲቪል ባለሙያ የሚመራ መንግሥት መመስረት፣ ምርጫ ለማካሄድ ብሔራዊ ምክክር መጀመር እና "ቀሪ የጦርነት አዝማሚያዎችን" ማስወገድ ሲሉ ወደ ዲሞክራሲ የሚወስዱ እርምጃዎችን ዘርዝረዋል።
◻ ንፁሃን ዜጎችን ለመጠበቅ እና የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነትን ለማመቻቸት ብሔራዊ እቅድ አቅርበዋል፤ ነገር ግን "በታጣቂ ቡድን ወንጀሎች ዙሪያ ያለውን ዓለም አቀፍ ዝምታ"፤ ማበረታቻ ሲሉ አውግዘውታል።
◻ ለሲቪል መንግሥት ምስረታ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ አሳስበዋል፤ "ያለ ሰላም፣ ዘላቂና የሚጭበጥ መጪ ገዜ አይኖርም። በፍጹም ተስፋ አንቆርጥም" ሲሉም አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X