አፍሪካ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ትልቅ ድምፅ ሊኖራት ይገባል ሲሉ የጋናው ፕሬዝዳንት አሳሰቡ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ትልቅ ድምፅ ሊኖራት ይገባል ሲሉ የጋናው ፕሬዝዳንት አሳሰቡ
አፍሪካ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ትልቅ ድምፅ ሊኖራት ይገባል ሲሉ የጋናው ፕሬዝዳንት አሳሰቡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.09.2025
ሰብስክራይብ

አፍሪካ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ትልቅ ድምፅ ሊኖራት ይገባል ሲሉ የጋናው ፕሬዝዳንት አሳሰቡ

ጆን ማሃማ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሲናገሩ "የተመድ ሚናውን እንደገና መገምገም፣ ይዘቱን እንደገና መወሰን እና መዋቅሮቹን እንደገና መቅረጽ አለበት" ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ዓለም አቀፉ ድርጅት "የዓለማችንን ኅብረ ብሄራዊ  ልዩነት በትክክል ማንጸባረቅ" እንዲሁም በሥልጣን አጠቃቀም ላይ በተለይም በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ "በአገሮች መካከል እኩልነትን" ማረጋገጥ አለበት ብለዋል።

ከሠላሳ ዓመታት በፊት ተመሳሳይ ጥሪዎች ከተደረጉ በኋላም ዛሬም "እኛ የአፍሪካ መሪዎች በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ የቬቶ (ድምጽን በድምጽ የመሻር) ሥልጣን ያለው ቋሚ መቀመጫ እንዲኖረን ተመሳሳይና ቀላል ጥያቄ አሁንም እያቀረብን ነው" ሲሉ ማሃማ የነገሩን ተመሳሳይነት ገልፀዋል።

"ስለዚህ ዛሬ እዚህ በተከበረው ቦታ ቆሜ ክብርት ፕሬዝዳንት፤  ዓለምን 'አሁን ካልሆነስ መቼ ነው?' ብዬ እጠይቃለሁ" ሲሉ ተናገረዋል። "እኛ የምንፈልገው የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ብቻ ሳይሆን፣ በአሁኑ ጊዜ አፍሪካን በሚጎዳ መልኩ የተደራጀውን የዓለም አቀፉ የፋይናንስ መዋቅርም እንደገና እንዲከለስ ጭምር ነው።" በማለት አጽናኦት ሰጥተዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0