ሩሲያ የሱዳንን የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ዘመናዊ እንደምታደርግ ሚኒስትሩ ገለጹ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ የሱዳንን የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ዘመናዊ እንደምታደርግ ሚኒስትሩ ገለጹ
ሩሲያ የሱዳንን የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ዘመናዊ እንደምታደርግ ሚኒስትሩ ገለጹ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.09.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ የሱዳንን የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ዘመናዊ እንደምታደርግ ሚኒስትሩ ገለጹ

የሩሲያ የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር አሌክሳንደር ኮዝሎቭ እንዳተናገሩት፤ የሱዳንን የባቡር መስመሮች፣ የባሕር ወደቦች እና የአየር ማረፊያዎች ለማሻሻል እንዲሁም የሲቪል አቪዬሽንና የባሕር ላይ ጉዞ ደህንነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ እርምጃዎችን ለማዘጋጀት የሁለትዮሽ የሥራ ማስፈጸሚያ ሰነድ ተፈርሟል።

ኮዝሎቭ ይህንን ያስታወቁት በሞስኮ የተካሄደውን 8ኛው የሱዳን እና የሩሲያ መንግሥታት የንግድና ኢኮኖሚ ትብብር ኮሚሽን ስብሰባ መጠናቀቅን ተከትሎ ነው።

ሁለቱ አገሮች የባንክ ባለሙያዎችን ለማሠልጠን እና በማዕከላዊ ባንኮቻቸው መካከል ትብብር ለማድረግ ተስማምተዋል።

በሩሲያ የግብርና ምርቶች ኤክስፖርት ምክንያት በሀገራቱ መካከል ያለው ንግድ ያደገ ሲሆን፤ ውይይቶቹ የንግድ እንቅስቃሴውን ብረታብረትን፣ ማዳበሪያዎችን፣ ማሽነሪዎችን እና መድኃኒቶችን እንዲጨምር ለማስፋፋት አቅጣጫዎችን አካተዋል።

የሱዳን ማዕድናት ሚኒስትር ኑራልዳይም ሞሐመድ አህመድ ጣሃ በበኩላቸው፣ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን በማጠናከር ረገድ ሩሲያ ላደረገችው ድጋፍ ከፍተኛ አድናቆት እንዳላቸው ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0