ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሳሕል አገሮችን ከማውገዝ ይልቅ በመደገፍ ይጠቀማል - ፕሬዝዳንት ብሪስ ክሎቴር ኦሊጊ ንጉማ

ሰብስክራይብ

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሳሕል አገሮችን ከማውገዝ ይልቅ በመደገፍ ይጠቀማል - ፕሬዝዳንት ብሪስ ክሎቴር ኦሊጊ ንጉማ

አፍሪካ ጥሬ ዕቃዎችን ብቻ እያቀረበች ሌሎች ዋጋቸውን ወስነው ትርፍ ሲያጋብሱ መቀበል የለባትም ሲሉ የጋቦን ፕሬዝዳንት ብሪስ ክሎቴር ኦሊጊ ንጉማ በኒው ዮርክ ተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተናገሩ፡፡

ፕሬዝዳንቱ የነሷቸው ተጨማሪ ሐሳቦች፦

ደህንነታችንን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ታይቶ በማይታወቅ የቴክኖሎጂ ልህቀቶች ቢኖሩም፣ ሰላም በተለይ በአፍሪካ እጅግ የራቀ ሆኖ ቀጥሏል።

ጋቦን በሳሕል፣ በአፍሪካ ቀንድ እና በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰላም እንዲሰፍን ጥሪ ታቀርባለች።

ጋቦን በኩባ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ ጥሪ ታቀርባለች፡፡

ጋቦን ለእስራኤልእና ፍልስጤም ግጭት የሁለት መንግሥታት መፍትሄን ትደግፋለች፡፡

ጋቦን የኮንጎ ተፋሰስ ዘብ ነች፣ ይህም የፕላኔታችን ሁለተኛው ትልቁ አረንጓዴ ሳንባ (መተንፈሻ) ሲሆን፣ ይህ አስደናቂ ቅርስ ለገንዘብ ስግብግብነት መሰዋት የለበትም፡፡

ደኖቻችን ለሰው ልጆች ለሚያቀርቡት ሥነ-ምሕዳራዊ አገልግሎቶች ፍትሐዊ ካሳ በሚሰጥበት ፍትሐዊ ዓለም አቀፍ አጋርነት ሊኖር ይገባል፡፡

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0