ሩሲያ 'የቴክኖሎጂ ቅኝ አገዛዝን' ትቃወማለች ሲሉ ፑቲን በሞስኮ የዓለም አቶሚክ ሳምንት ላይ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ 'የቴክኖሎጂ ቅኝ አገዛዝን' ትቃወማለች ሲሉ ፑቲን በሞስኮ የዓለም አቶሚክ ሳምንት ላይ ተናገሩ
ሩሲያ 'የቴክኖሎጂ ቅኝ አገዛዝን' ትቃወማለች ሲሉ ፑቲን በሞስኮ የዓለም አቶሚክ ሳምንት ላይ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.09.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ 'የቴክኖሎጂ ቅኝ አገዛዝን' ትቃወማለች ሲሉ ፑቲን በሞስኮ የዓለም አቶሚክ ሳምንት ላይ ተናገሩ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት በፎረሙ ባደረጉት ንግግር ከኑክሌር ኃይል ጋር በተያያዘ የሰጧቸው ሌሎች ቁልፍ ሐሳቦች

  ተንሳፋፊ የኑክሌር ኃይል ማመንጫዎች፤ ሩሲያ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተንሳፋፊ የኑክሌር ኃይል ማመንጫዎችን በጅምላ ማምረት ትጀምራለች።

የተዘጋ የነዳጅ ዑደት፤ በዓለም የመጀመሪያው የሆነው የተዘጋ የነዳጅ ዑደት ያለው የኑክሌር ኃይል ሥርዓት እ.ኤ.አ. እስከ በ2030 ሩሲያ ውስጥ ለማስጀመር ታቅዷል።

  ዓለም አቀፍ ፍላጎት፤ በሩሲያ ዲዛይን የተሠሩ የኑክሌር ኃይል ማመንጫዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው።

ሰላማዊ አጠቃቀም እና የኑክሌር ጦር መሳሪያ  መስፋፋትን መከላከል፤ ሰላማዊ የኑክሌር ኃይል ልማትን ከኒውክሌር የጦር መሳሪያ መስፋፋትን መከላከል አሰራር  ጋር ማመጣጠን ወሳኝ ነው።

ፋይናንስ ፤ የኑክሌር ኃይል ማመንጫዎችን ለመገንባት አዳዲስ የፋይናንስ ሞዴሎች ያስፈልጋሉ።

  የሀብት አመለካከት፤  የዩራኒየም ሀብቶች እስከ 2090 (እ.ኤ.አ.) ድረስ ሊያልቁ ይችላሉ ተብሎ ታቅዷል፤ ምናልባትም ከዚያ ቀደም ብሎ።

ደህንነት ፤ ከማዕድን ማውጣት እስከ ማብለያ ሥራ ድረስ ባለው የኑክሌር ዑደት ደረጃ ሁሉ ከፍተኛ የደህንነት መስፈርት ያስፈልጋል።

ዓለም አቀፍ ልማት፤  ለሰላማዊ የኒውክሌር ኃይል ቴክኖሎጂዎች እኩል ተደራሽነት ለዘላቂ ዓለም አቀፍ ልማት በጣም አስፈላጊ ነው።

የኑክሌር ደህንነት ቅድሚያ፤ የኃይል ማመንጫ ተቋማት የትም ቦታ ቢሆኑ የኑክሌር ደህንነታቸውን ማረጋገጥ ለሩሲያ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።

የረጅም ጊዜ ፕሮጀክቶች፤ ሩሲያ የረጅም ጊዜ የኑክሌር ፕሮጀክቶችን የማስተዳደር ፍላጎት አላት።

  ዓለም አቀፍ ትብብር፤ ሰላማዊ የኑክሌር ቴክኖሎጂዎች ለዓለም አቀፍ ትብብር እና በአገሮች መካከል ለሚደረግ የጠበቀ ግንኙነት መሠረት ናቸው።

  የልማት አጋሮች፤  ሩሲያ የኑክሌር ኃይል አጋሮቿ የላቀ የልማት እድገት እንዲያገኙ ትረዳለች።

  ሉዓላዊ የኑክሌር ኢንዱስትሪ፤ ሩሲያ የቴክኖሎጂ ቅኝ አገዛዝን በመቃወም እና የውል ግዴታዎችን በጥብቅ በመከተል አጋሮቿ የራሳቸውን ነጻ የኑክሌር ኢንዱስትሪዎች እንዲገነቡ የመርዳት እቅድ አላት።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0