ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ትብብሯን ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን ተናገሩ
18:12 25.09.2025 (የተሻሻለ: 18:24 25.09.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ትብብሯን ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን ተናገሩ
የኑክሌር ኃይል ለሀገሪቱ የረጅም ጊዜ ልማት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
“የኑክሌር ኃይል የረጅም ጊዜ ልማትን ለማረጋገጥ፣ የኃይል ምንጫችንን ለማስፋት እና የኢትዮጵያን አቅም እውን ለማድረግ ወሳኝ ነው። ግባችን ግልጽ ነው፤ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የኃይል ምንጭን የሚያሰፋ እና የኢትዮጵያን አቅም እውን የሚያደርግ የኑክሌር መርሃ ግብር ነው።” ብለዋል፡፡
ሩሲያ ሳይንስ ከራዕይ ጋር ሲስማማ ምን ሊያሳካ እንደሚችላ አሳይታለች ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያና ሩሲያ በጋራ እያካሄዷቸው ያሉ ፕሮጀክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
በኢትዮጵያ የኑክሌር መሠረተ ልማት መገንባት።
ለኑክሌር ዘርፉ ሠራተኞችን ማሰልጠን።
ለኑክሌር ኃይል የቁጥጥር ማዕቀፎችን ማጠናከር።
የኑክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል ማቋቋም።
የኑክሌር ሳይንስን ለሰላማዊ አጠቃቀሞች ትብብር ማስፋፋት።
በቴክኖሎጂ ሽግግርና ደህንነት ስልጠና ዙሪያ አጋርነት መፍጠር።
ሮሳቶም የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል ሲሉ የሮሳቶም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት ባላቸው ዕቅድ ላይ ተናግረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X