የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ በኒው ዮርክ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው ሌሎች ሃሳቦች ፦

ሰብስክራይብ

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ በኒው ዮርክ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው ሌሎች ሃሳቦች

የአየር ንብረት ለውጥ በታዳጊ አገራት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው።

ሶማሊያ ጨምሮ ሌሎች ታዳጊ መንግስታት የመቋቋም አቅም እና የልማት ግቦቻችንን የሚያደናቅፉ ከባድ የፋይናንስ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ እየተገደዱ ነው።

በኢንዱስትሪ የበለጸጉ አገራት ለአየር ንብረት ቀውስ የገቡትን የፋይናንስ ግዴታዎች በአስቸኳይ መወጣት ወሳኝ ነው፤ ቸልተኝነታቸው ሁኔታውን እያባባሰው ይገኛል።

"ሶማሊያ ለዓለም አቀፉ የካርቦን ልቀት ምንም አይነት አስተዋፅኦ የላትም፤ ሆኖም ግን እጅግ የከፋ መዘዞችን እየተቀበልን ነው። ድርቅ፣ ጎርፍ እና የባሕር ከፍታ መጨመር የኑሮ ምንጮችን እያጠፉና ቤተሰቦችን እያፈናቀሉ ነው።"

ሶማሊያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠናን የመቀላቀል የምትደርገው ሂደት 'በጣም ጥሩ' እየሄደ ነው።

ሶማሊያ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና የካፒታል ገበያዎች በቀላሉ የሚገኝ፣ ተመጣጣኝ፣ ሊገመት የሚችል እና ፍትሃዊ የሆነ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ታሳስባለች።

እንደ ሶማሊያ ያሉ የአየር ንብረት ቀውስ ግንባር ቀደም የሆኑ አገራት፣ እያጋጠማቸው ያለውን አስቸኳይ ተግዳሮቶች ለመቋቋም ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ማዕቀፍ በቂ ድጋፍ ሳያገኙ ብቻቸውን እንዲጋፈጡ ሊተዉ አይገባም።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0