በሰው ሠራሽ አስተሎት እና ሮቦቲክስ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞችን ለማስጀመር የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሰው ሠራሽ አስተሎት እና ሮቦቲክስ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞችን ለማስጀመር የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
በሰው ሠራሽ አስተሎት እና ሮቦቲክስ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞችን ለማስጀመር የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.09.2025
ሰብስክራይብ

በሰው ሠራሽ አስተሎት እና ሮቦቲክስ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞችን ለማስጀመር የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

ስምምነቱን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሥራ ኃላፊዎች ተፈራርመዋል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ወርቁ ጋቸና "ይህ ስምምነት ዘርፉን በመጀመሪያ ዲግሪ በመስጠት ደረጃ ቀዳሚ ያደርገዋል ያሉ ሲሆን ተግባራዊ ለማድረግ በሚኖረዉ ሥራም ከፍተኛ ጥረት እናደርጋለን" ብለዋል።

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር እንደተናገሩት፤ ሥርዓተ ሥልጠናው ተዘጋጅቶ በመጠናቀቁ በዚህ ዓመት ይጀመራል።

"ስምምነቱ ለኤ.አይ(ሰው ሠራሽ አስተውሎት) እና ለሮቦቲክስ ኢንተለጀንት ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች የሰው ኃይል ፍላጎትን ለማሟላት ትልቅ እገዛ ይኖረዋል" ማለታቸውን የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃ ይጠቁማል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0