ነቀምቴ ከተማ ውስጥ አንዲት እናት 5 ልጆችን በአንድ ጊዜ ተገላገለች
14:46 25.09.2025 (የተሻሻለ: 14:54 25.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ነቀምቴ ከተማ ውስጥ አንዲት እናት 5 ልጆችን በአንድ ጊዜ ተገላገለች
የነቀምቴዋ ነዋሪ አስቴር ተረፈ፣ ሦስት ወንድና ሁለት ሴት ልጆችን በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ኮንፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሰላም ተገላግላለች፡፡ እናትና የተወለዱት አምስት ሕጻናት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ሆስፒታሉ አሳውቋል፡፡
አስቴር ከወሊድ በኋላ በሰጠችው አስተያየት፤ ከአምስት ዓመት በፊት ከወለደቻት ሴት ልጇ በስተቀር ሌሎች ልጆች እንዳልነበሯት በማስታወስ፣ ሕፃናቱ በሰላም በመገላገሏ ደስታቸዋን ገልፀዋል።
ባለቤቷ ተመስገን ዓለሙ በበኩሉ፣ ቤተሰቡ በደስታ የተዋጠ ቢሆንም፣ በአንዴ አምስት ልጆችን ማሳደግ ፈታኝ እንደሚሆን ገልጾ፣ የአራስ ልጆቹን ፍላጎት ብቻውን ማሟላት አስቸጋሪ ስለሚሆን ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ