ኢትዮጵያ እና ኬንያ ከ62 ዓመታት በኋላ ሁለተኛውን ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
13:08 25.09.2025 (የተሻሻለ: 13:14 25.09.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ኬንያ ከ62 ዓመታት በኋላ ሁለተኛውን ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኬንያ መከላከያ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ቻርልስ ሙሪዩ ካሃሪሪ፣ በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ የሁለትዮሽ ውይይት ካደረጉ በኋላ በጋራ መሥራት በሚቻልባቸው መስኮች ላይ ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል ።
እ.ኤ.አ በ1963 ኬንያ ነፃነቷን ባገኘችበት ዓመት የታህሳስ ወር መጀመሪያ የተፈረመውን ስምምነት ተከትሎ የተፈረመው ሁለተኛው ስምምነት፦
🟠 የጋራ ወታደራዊ ልምምድ፣
🟠 ሥልጠና በወታደራዊ ኢንዱስትሪ፣
🟠 ሽብርተኝነትን መዋጋት፣
🟠 በድንበር ደህንነት እና በሌሎችም ተያያዥነት ያላቸው ወታደራዊ ጉዳዮች ያካተተ ነው፡፡
የኬንያ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ቻርልስ ሙሪዩ ካሃሪሪ፣ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ያደረጉት ወታደራዊ ስምምነት ከሁለቱ ሀገራት ባለፈ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋትም የጎላ ፋይዳ እንዳለው ገልፀዋል ማለታቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
