የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒ በ80ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች
የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒ በ80ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች
ዓለም አቀፍ ፈተናዎች የጎርጎሮሳውያኑ 2030 ዘላቂ ልማት ግቦችን አደጋ ላይ እየጣሉ ነው። በተለይም እየጨመረ የመጣው የእኩልነት ያለመስፈን እና በተለይም በፍልስጤም እየደረሰ ያለው አሳዛኝ ክስተት ቀጥሏል።
ኮሞሮስ ለፍልስጤምዋና ከተማዋም ምስራቅ እየሩሳሌም ሆኖ የሁለት መንግሥታት መፍትሄ መሰጠቱን ትደግፋለች፤ እንዲሁም ለፍልስጤም በቅርቡ እውቅና የሰጡትን ፈረንሳይና ሌሎች ሀገራት አድንቃለች።
በዓለም አቀፍ አስተዳደር ላይ የበለጠ ፍትሕ እና ተሳትፎን ለማሳደግ አፍሪካ የፀጥታው ምክር ቤት ያላት ውክልና መረጋገጥ አለበት።
ኮሞሮስ ፈረንሳይ ማዮቴን መያዟን አውግዛለች፤ እንዲሁም ይህን ዘላቂ ጉዳይ ለመፍታት በዓለም አቀፍ ሕግ ላይ የተመሠረተ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ በድጋሚ አሳስባለች።
እንደ ኮሞሮስ ካሉ ትናንሽ ደሴታማ ሀገራት የሚነሱ የባህር የውኃ መጠን እና ከከፍተኛ የአየር ሁኔታ አደጋዎች ጋር እንዲዋጉ ለመርዳት የአየር ንብረት ፋይናንስን ለማስጠበቅ አስቸኳይ እርምጃ ያስፈልጋል።
ኮሞሮስ የብሔራዊ ልማትን ለማስኬድ በኢኮኖሚ ዕድገት፣ በኃይል ሽግግር እና በሰማያዊ ኢኮኖሚ ላይ የሚያተኩረውን 'ፕላን ኮሞረስ ኢመርጀንት' የተሰኘ ዕቅዷን በማስኬድ ላይ ትገኛለች።
ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ከአየር ንብረት ቀውሱ በኋላ፤ የተሻሻለ ፍትሃዊ የሆነ ዓለም አቀፍ ሥርዓት እንዲገነባ የተስተካከለ ብዝኃነት ያለው ስረዓት እንዲሁም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ መዋቅር ማሻሻያዎች መተከል አለባቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X