"በአፍሪካ ላይ የደረሰውን ኢፍትሐዊነት ለማስተካከል ጊዜው አሁን ነው" ሲሉ የማዕከላዊት አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አሳሰቡ

ሰብስክራይብ

"በአፍሪካ ላይ የደረሰውን ኢፍትሐዊነት ለማስተካከል ጊዜው አሁን ነው" ሲሉ የማዕከላዊት አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አሳሰቡ

በፋውስቲን አርቼንጅ ቱዋዴራ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤንግግር ያነሷቸው ቁልፍ ጉዳዩች

በዓለም ሰሜናዊ ክፍል ሃብት እየተከማቸ ባለበት ወቅት በአፍሪካ ድህነት እየተባባሰ መምጣቱ ተቀባይነት የለውም።

"የነገው አኅጉር እንደ ትናንቱ አኅጉር እየተቆጠረ ባለበት ወቅት ስለ ዓለም አቀፍ ደህንነት እና ፍትሕ ማውራት አይቻልም።"

አፍሪካ የፀጥታው ምክር ቤት የቬቶ (ድምጽን በድምጽ የመሻር) መብት ያላቸው ሁለት ቋሚ መቀመጫዎች ሊኖራት ይገባል። "ይህ እንደ ምጽዋት ሳይሆን እንደ ፍትሕ፣ እንደ ልዩ መብት ሳይሆን እንደ አስፈላጊነት መታየት አለበት።"

ቱዋዴራ የተመድ የቅድመ መከላከል ዲፕሎማሲ ስልቶችን ለማጠናከር በዋና ኃይሎች በሚደገፍ እና በግልጽ በሚተዳደር 'ዓለም አቀፍ ግጭት መከላከል ፈንድ' እንዲቋቋም ሐሳብ አቅርበዋል።

በተጨማሪም የአካባቢ ግጭቶች ወደ ግልጽ ጦርነት እንዳያድጉ ለመከላከል ተመድ የሚያደርገውን ጥረት ማሟላት የሚችሉ የክልላዊ አሸማጋዩች ጥምረቶች በትከክለኛ መንገድ እንዲቋቋሙ ጠይቀዋል።

በአፍሪካ የሰላም ማስከበር ሥራዎች የፋይናንስ ድጋፍ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በግዴታ መዋጮዎች ላይ ተመሥርቶ መዋቅራዊ እና ቀጣይነት ያለው እንዲሆን አሳስበዋል።

በዲጂታል ዓለም የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ እንዲረጋገጥ "የዲጂታል አስተዳደር እና የሥነ-ምግባር ሰንሰለታዊ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ዓለም አቀፍ ቻርተር" እንዲፈጠር ሐሳብ አቅርበዋል።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0