የኢትዮጵያ 71 ከተሞች "ስማርት" ከተማ ለመሆን ጉዞ ጀምረዋል - የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ 71 ከተሞች "ስማርት" ከተማ ለመሆን ጉዞ ጀምረዋል - የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር
የኢትዮጵያ 71 ከተሞች ስማርት ከተማ ለመሆን ጉዞ ጀምረዋል - የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.09.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ 71 ከተሞች "ስማርት" ከተማ ለመሆን ጉዞ ጀምረዋል - የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ወደ "ስማርት " ከተማነት ማደጓ የኮንፈረንስ ማዕከል እንድትሆን እድል ከፍቶላታል ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታ ፈንታ ደጀኔ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

"ስማርት ሲቲ ሲባል በኢትዮጵያ አገባብ "ስማርት" ኢኮኖሚን፣ አካባቢን ፣ ሕዝቡን፣ የኑሮ ደረጃን እንዲሁም የእንቅስቃሴ መስፈርቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው" ሲሉ ስለ "ስማርት" ከተሞች ወጥ የሆነ አረዳድ አለመኖሩን አስረድተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው፣ በዚህ የከተሞች ሽግግር ወቅት ቅርሶችን በተመለከተ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉን አንስተዋል።

"ለሀገሪቱ እና ለሕዝብ የሚጠቅሙ ሕንጻዎችና ቅርሶች አልተነኩም ... ለምሳሌ ጎንደር የፋሲል ግንብን መውሰድ ይቻላል፤ አባ ጅፋርን መውሰድ ይቻላል። ከነበሩበት የበለጠ ጎልተው እንዲታዩና ቅርስነታቸው ጎልቶ እንዲታይ ነው የተደረገው" ሲሉ አጠቃልለዋል።

ሀገሪቷ ካሏት 2543 ገደማ ከተሞች (አብዛኞቹ የገጠር ከተሞች)፣ አቅም ያላቸው እና መሥራት የሚችሉ ከተሞች የስማርት ከተማነት ጉዞ መጀመራቸውንም ገልፀዋል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0