ዓለም በተባበሩት መንግድሥታት ላይ “ተስፋ መቁረጥ” የለበትም - የኬንያው ፕሬዝዳንት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዓለም በተባበሩት መንግድሥታት ላይ “ተስፋ መቁረጥ” የለበትም - የኬንያው ፕሬዝዳንት
ዓለም በተባበሩት መንግድሥታት ላይ “ተስፋ መቁረጥ” የለበትም - የኬንያው ፕሬዝዳንት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.09.2025
ሰብስክራይብ

ዓለም በተባበሩት መንግድሥታት ላይ “ተስፋ መቁረጥ” የለበትም - የኬንያው ፕሬዝዳንት

ዊልያም ሩቶ በንግግራቸው ያነሷቸው ተጨማሪ ሐሳቦች ፦

ኬንያ ወታደራዊ መፍትሔ እንደሌለና ብቸኛው ትክክለኛ መንገድ የፖለቲካ ውይይት እንደሆነ በማረጋገጥ ግብፅን፣ ሳውዲ አረቢያን፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች እና አሜሪካን አካትቶ ለሚመሰረተው “የጥበቃ ቡድን” ሙሉ በሙሉ ድጋፍ ትሰጣለች።

"ሱዳንን ለመከፋፈል የሚደረጉ ማናቸውንም ሙከራዎች አጥብቀን እንቃወማለን፤ የሱዳንን ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና የግዛት አንድነት እንዲያከብሩ የሱዳን ጦር፣ የፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች እና የውጭ ተዋናዮችን ጨምሮ ሁሉንም  አካላት በማሳሰብ "የጥበቃ ቡድኑን" እንቀላቀላለን።

አሁን ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ደሃ አገሮችን “ይቀጣል”፣ ሀብታም አገሮችን ደግሞ “ይሸልማል”።

"የዓለም የልማት ፋይናንስ ተቋማት የብዝሃ-ዋልታ ዓለምን በተለይም የድሃ እና ታዳጊ አገሮችን ፍላጎት ማሟላት አልቻሉም።"

ይሁን እንጂ አፍሪካ “የውጭ ሐኪም ትዕዛዝን እየጠበቀች” አይደለም፤ ይልቁንም “የፋይናንስ ነፃነቷን ለማጠናከር፣ መረጋጋቷን ለማስጠበቅ እና ልማትን ለማፋጠን በደፍረት እና ታቅዶበት የተወሰዱ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው”።

አፍሪካ ከፀጥታው ምክር ቤት መገለሏ “ተቀባይነት የሌለው፣ ኢ-ፍትሃዊ እና እጅግ ልክ ያልሆነ ብቻ ሳይሆን፣ የተባበሩት መንግሥታት መልካም ስምንም ያዳክማል”።

  ዓለም በተመድ ላይ “ተስፋ መቁረጥ” የለበትም ፤ ይልቁንም “ለዓላማው እንዲመጥን፣ አወቃቀሩን ማሻሻል” አለበት።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0