ናይጄሪያ የቻይናን ዓለም አቀፍ የአስተዳደር ተነሳሽነት፣ ፍትሐዊ እና ሁሉን ያካተተ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ለመፍጠር ያስችላል ስትል ሙሉ ድጋፍ መስጠቷን ባለሥልጣኑ አሳወቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱናይጄሪያ የቻይናን ዓለም አቀፍ የአስተዳደር ተነሳሽነት፣ ፍትሐዊ እና ሁሉን ያካተተ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ለመፍጠር ያስችላል ስትል ሙሉ ድጋፍ መስጠቷን ባለሥልጣኑ አሳወቁ
ናይጄሪያ የቻይናን ዓለም አቀፍ የአስተዳደር ተነሳሽነት፣ ፍትሐዊ እና ሁሉን ያካተተ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ለመፍጠር ያስችላል ስትል ሙሉ ድጋፍ መስጠቷን ባለሥልጣኑ አሳወቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.09.2025
ሰብስክራይብ

ናይጄሪያ የቻይናን ዓለም አቀፍ የአስተዳደር ተነሳሽነት፣ ፍትሐዊ እና ሁሉን ያካተተ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ለመፍጠር ያስችላል ስትል ሙሉ ድጋፍ መስጠቷን  ባለሥልጣኑ አሳወቁ

የናይጄሪያ-ቻይና ስትራቴጂክ አጋርነት ዋና ዳይሬክተር  ጆሴፍ ቴግቤህ የናይጄሪያውን ፕሬዝዳንት በመወከል እንደተናገሩት ፤ የዓለም አቀፍ የአስተዳደር ተነሳሽነት (ጂጂአይ) ራዕይ ከቦላ ቲኑቡ የ'ለውጥ ተስፋ' አጀንዳ ጋር በጥብቅ የተጣጣመ ሲሆን ይህም፦

ኢኮኖሚውን በማነቃቃት፣

ማህበራዊ  ሁሉን አካታችነት እና

ንቁ ዓለም አቀፍ ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ነው።

ቴግቤህ አክለውም ጂጂአይ በሉዓላዊ እኩልነት፣ በዓለም አቀፍ ሕግ እና በብዝኃነት ትብብር ላይ ማተኮሩ የናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዩች ጋር የሚስማማ ነው።

የጂጂአይ ሀሳቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

🟠 አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ተወካይ እንዲኖራት የምታደርገው ጥረት፣

🟠 ሰላም የማስከበር ጥረቶች፣

🟠 በምዕራብ አፍሪካ ውስጥ ለሚካሄደው ግጭት እልባት ቁርጠኝነት እና

🟠 በኢኮዋስ፣ በአፍሪካ ሕብረት እና በተባበሩት መንግሥታት አማካኝነት የጋራ እርምጃን ማበረታታት።

በተጨማሪም ተነሳሽነቱን "ለተግባር የቀረበ ጥሪ" ሲሉ ገልፀው ፤ ለዜጎቿ፣ ለአፍሪካ እና ለዓለም ማኅበረሰብ የሚታይ እድገት ለማምጣት ከቻይና እና ከሌሎች አጋሮች ጋር ለመተባበር ናይጄሪያ ያላትን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0